INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የሰላሙ ሂደት ከአረም የፀዳ አይደለም!

ከሁለት አመት በላይ የተካሄደውና በትግራይ ላይ የተከፈተው የአለማችን አስከፊው ጦርነት በሰላም ለመፍታት በቅርቡ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ለተግባራዊነቱ ጥረት እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ በአማራ ህዝብ ስም የሚነግዱት ተስፋፊ ሃይሎች አሁንም ወደ ሌላ አስከፊ ችግር ሊያሸጋግሩት ይኸውና ሰሞኑን በፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ውል አንቀበልም፤ በህገ-መንግስትም አንገዛም በማለት ዛሬ በአዲስ መልክ በተደራጀው የፋኖ ወኪላቸው አማካይነት መግለጫ ሰጥተዋል።

ከመጀመሪያውም ቢሆን በኢትዮጵያ የተፈጠረው የህብረ-ብሄራዊ ስርአትና የተጀመረው የሰላምና የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እድገት አንቀበልም ብለው ላለፉት አመታት በውስጥና በውጭ አገር መሽገው በህዝቦች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር ሲሰሩ የነበሩ ፤ በአሁኑ ጦርነት በሽዎች ዘምተው በትግራይ ህዝብ ላይ ታሪክ የማይረሳው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙና የትግራይ ህዝብ ከቀየው ነቅለው፤ መሬቱናን ንብረቱን ዘርፈው ለስደት ከዳረጉ በሃላ እስከ አሁን ድረስ መሬቱን በወረራ ይዘው ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ ሃይሎች ናቸው።

በየመድረኩ ስምና ቀለማቸው እየቀያየሩ "በኢትዮጵያ አንድነት" ስም ብሄር-ብሄረሰቦች ሲያንቃሽሹና ህገመንግስቱ አይወክለንም እያሉ ሰርአቱን በሃይል ለመናድ ከአስመራው ኢሳያስና መሰሎቹ ጋር በትጥቅ ትግል ሳይቀር አገር ለማፍረስ ሲሰሩ የነበሩ፤ በሌላ በኩል ከሚጠተየፍዋቸው የብሄር ፖለቲካ አራማጆች ጋር በመመሳጠር የተምታታ አላማ-ቢስ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሲያራምዱ የቆዩት እነዚህ ሃይሎች አገሪትዋ አሁን ለገጠማት የተወሳሰበ ችግርና የህዝቦች እልቂት ተጠያቂዎች ናቸው።

ለሰላሙ ሲባልም ቢሆን እውነቱ መናገር ይበጃልና ፋኖዎች የመንደር ሽፍቶች ሳይሆኑ የተስፋፊው ሃይል የአመለካከት ውጤት ናቸው። ፋኖዎች ከመንደር ወረበላ እስከ ጡረተኛ ጄነራል፤ ከግማሽ ትግራይ የወልቃይት ተወላጅ እስከ የአሜሪካ ነዋሪ የአማራ አቀንቃኝ ተቀናጅቶ የሚሰራ፤ በአንድ በኩል "ኢትዮጵያዊ" ነኝ በሌላ በኩል "የአማራ ብሄረተኛ" ነኝ የሚሉ ሃይሎች ሁለ የአስተሳሰብ ውጤት ናቸው። ትላንትና በትግራይ ህዝብ ላይ ጥላቻ ሲሰብኩና የአሁኑ የለውጥ ሃይሎች አካል ነን የሚሉት ተስፋፊዎች፤ በአንድ በኩል በአዲስ አበባ በመንግስት ጉያ በአማካሪነትና በመሪነት ተሸጉጠው የትግራይ ህዝብ ታሪክ እስከ ወዲያኛው እንዳይታወስ እናደርጋለን፤ ለመቶ አመት ወደህዋላ መልሰናቸዋል ሲሉ የቆዩ፤ በሌላ በኩል ከኢሳያስ ቡድን አዲስ የጥፋት ቀልበት አጥልቀው በተለይም በምእራብ ተግራይ ተነግሮ የማያልቅ ጆኖሳይድ የፈፀሙ ሃይሎች ናቸው። ከብዙ በጥቂቱ የአማራ ሃይሎች የተምታቱና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ፍላጎቶች ምንድናቸው?

የሚሉትን እንጠቁም፡

1ኛ/ የአማራ ሃይሎች የአሁኑ የለውጥ ሃይል አካል ነን ብለው የአዲስ አበባው ስልጣን ተቆናጥዋል፤ ከተወካዮች ምክርቤት እስከ ፌዴሬሽን አፈጉባኤነት፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት እስከ ቀበሌ የሚመሩዋቸው ባለስልጣናት አሁን ባለው ህገ-መንግስት መርጠው ተቀብለዋል። የትግራይ ህዝብን ምርጫ አውግዘው የአማራ ክልል አስተዳደርና መንግስት አለን ብለው የጥምር ጦር አካል ሆነን ትግራይ ዘምተን ብዙ መስዋእትነት ከፍለናል የሚሉ ሃይሎች፤ መልሰው በአገሪቱ ህገመንግስት አንገዛም ማለት ምን ማለት ነው? የሚገዙት "በኤርትራ ህገመንግስት" ካልሆነ በስተቀር። በአንድ በኩል የወሰንና የማንነት ኮሚሽን ሰይመናል ሲሉን ቆይተው፤ የእርቅና የሰላም ኮሚቴ መርጠናል ሲሉን ከርመው ፤ ለዚህም "ጅብ በልተን እንቀድስ' የሚሉ ወኪሎቻቸውና ሲመች ጦር ሜዳ ወርደው የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ሰራዊት የመረቁ፤ ከሊቁ እስከ ሊህቁ በአንድ አገር ህዝብ ላይ ለሁለት አመታት በረሃብ እንዲያልቅ የፈረዱ፤ በሌላ በኩል የሰላም ልኡካን ነበርን የሚሉ ሃይሎች እጅ ያለበት የአማራ ሃይሎች እንቅስቃሴ ግራ የተጋባ ወይስ ከጥፋት የማይማር አሜኬላ? መልሱ ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ጦርነት የደረሰበትን ኪሳራ እንዲያበቃ ውሳኔ ላይ ደርስውዋል፤ ነገር ግን ከአረም ነፃ አይደለም፡

2ኛ/ የእነዚህ ሃይሎች ርእዮት ምንድነው? ኢትዮጵያዊነት? አማራነት? ወይስ ሁለቱም? የነዚህ ጥያቄዎች መምታታት የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች የሚል ፍረጃ አሰጥተዋቸዋል። ለምን ቢባል ሦስቱም አማራጮች በህገመንግስቱ መፍትሄ ተበጅቶላቸዋል። ይህን ህገመንግስት ባይመቸንም እስኪሻሻል ወይም እስኪ ሰረዝ ድረስ አብረን በሰላም ችግራችን እንፍታ ማለት ችግሩ ምንድለው? እውነቱን እንነጋገርማ ከተባለ፤ በሰላሙ ስምምነት የተካተቱ አንቀፆች ለትግራይ ህዝብ የሚመቹ አይደሉም፤ በጀግንነቱ የታጠቀውን እንዲፈታ የሚጠይቅ፤ በ3 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠውን መንግስት የማይቀበል፤ በትግራይ ህዝብ ላይ የተሰራውን ወንጀል በሃላፊነት የሚጠየቁ ሃይሎች የሚዳኙበት ስርአት ያላበጀ ወዘተ የሚሉ አንቀፆች ያሉበት፤ የተበዳዩን ለበዳይ የሰጠ " ፍርደ ገምድል" ነው። ያም ሆኖ የትግራይ ህዝብና መሪዎች አንቀበልም አላሉም ይልቁንስ ከጦርነት ውጭ፤ በቀለለ መስዋእትነት በፖለቲካ መፍትሄ እናገኛለን፤ ድሮውም ተገደን የገባንበት ጦርነት ነው፡ የሰው ህይወት ከሚጠፋ በገደለን ህገመንግስም ቢሆን እንዳኝ ብሎ ተቀብሎታል። ስለዚህ የአማራ ሃይሎች ሲመቻቸው መከላከያ የኛ ነው ሲሉን ቆይተው አሁን መከላከያና የትግራይ ሃይሎች ተኩስ እናቆማለን ሲሉ ፋኖ እንተኩሳለን ማለት ምን ማለት ነው? ፤ ነገሩ ከፋኖ በላይ ነው።

በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች እያናቆሩ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው እነዚህ ሃይሎች በቃችሁ መባል ያለበት ጊዜ አሁን ነው። የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ክልል ህዝቦችም ተመሳሳይ ሁኔታ እየተፈጠረ ያለው በያዙት የተምታታ አመለካከት ነው። የአሃዳዊ ስርአት ለመመለስም ይሁን የአማራ ቤሄረተኝነት ለመጀመር ማጠንጠኛው ሰላምዊ ትግል እንጂ፤ "ሲሞቅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ" እንድሚባለው፤ አንዴ እኔ ብቻ ነኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ፤ ሌላ ጊዜ አማራ ለብቻው ተጎድተዋልና የአማራ ብሄረተኛ ንኝ እያሉ ማምታታት ለነሱም ለአማራ ህዝብም አልበጀምና፤ ካለፉት ሁለት የጦርነት አመታት ያገኙትን ትርፍና ኪሳራ አስልተው እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ችግራቸው በውይይት ቢፈቱና ወደ ሰላማዊ ትግሉ ቢቀላቀሉ ይሻላል። አለበለዚያ " አረም ናችሁ" ተብለው እንዳይነቀሉ ስጋት አለኝ።