INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የየካቲት ወግ

ደጃዝማች ትራምፕና ግራዝማች ባይደን በተፋለሙበት ዘመን አለም የሁለቱን ፍልሚያ ውጤት ለመስማት በጉጉት ተወጠረች፣ይህንን ተከትሎም አንዳች ዱብዳ ይገጥመኛል ብላ ተጨነቀች፣ተጠበበች።አለም ጆሮዋንም ልቧንም ቀስራ ከሀሳቧ ጋር በነጎደችበት ቀን ብልጽግና የሚባሉ አገር አፍራሾች፣በመሪያቸው አማካይነት በገዛ ህዝባቸው ላይ በውድቅት ሌሊት አራት የውጭ አገር ጠላት ጋብዘው ጦርነት አወጁ።

አለም በምርጫ፣አበሾች በጥላቻ ናላቸው በዞረበት ሰአት ለማየት የሚዘገንኑ፣ለመስማት የሚሰቀጥጡ ግፎች በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈጸመ።በዚያን ጊዜ ከጥቂት አካላት በስተቀር የንጹሀን ጉዳት የሚሰማው፣የምስኪኖች ቁስል የሚያመው፣የዜጎች ጥቃት የሚየንገበግበው፣ብሄራዊ ክብር የሚመለከተው ጠፋ።አባቶች፣ምሁራን፣ጋዜጠኞች፣የሰብአዊ መብት ጠበቆች ባልሰማ ባላየ ዝም ጭጭ አሉ፣አንዳንዶች አበጃችሁ የኛ ልጆች ብለው አጨበጨቡ፣እንዳንዶቹ ደግሞ መስቀል ሱናቸውን፣ስነምግባር ሞያቸውን ሸምጥጠው እነሱም ሊፋጁ ነፍጥ ጨበጡ።አገር ተደፈረች፣ታጋይ ስዬ እንዳለው እንደዛው የኮማሪት ቤት ሆነች።

ትግራዮች የታሪካቸውን ትልቁን ስህተት ተሳሳቱ፣ኢትዮጵያን አመኑ፣ህወሀታዊ ኢትዮጵያ ሄዳ ብልጽግናዊ ኢትዮጵያ ብትመጣ ትግራይነትን የሚያጠቃ አይመጣም አሉ፣ህወሀትን ሸኝተው ብልጽግናን ተቀበሉ።ብልጽግና ግን በማር የተለወሰ መርዟን ተፋች፣የጥፋት ሰይፏን፣የፍጅት ሳንጃዋን ከሰገባው አወጣች።ህጻን አዋቂ ሳትል፣ሲቪል ከፖለቲከኛ ሳትመርጥ፣ጾታ ሀይማኖት ሳትል ትግራዋይ የሆነውን ሁሉ መናደፍ ጀመረች።ህዝብን አስነወረች፣የራሷ አላረካት ብሎ ሌሎች ግፈኞችን የግፍ ጽዋ እንዲያነሱ ጋበዘች።

የትግራይ ህዝብ ስህተቱ ገባው፣ያመነው አራጁን መሆኑን አሰበ።ጠባቂው፣አታጋዩ መሪው፣ተከላካዩ እንዲህ ካለ ክፉ ጊዜ የሚያስጥለው ቤዛው #ህወሀት እንጅ ብልጽግና እንዳልሆነ፣የራሱ ክንድ እንጅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዳልሆነ ተረዳ።ወደ ምድረበዳ ወረደ፣ ታደሰ ወረደን ፈለገ፣ደብረጥዮንን መረቀ፣ጻድቃንን አደመጠ፣ምግበይን አስቀደመ፣ድንኩልን ተከተለ፣ጌታቸውን አናገረ፣ብንያምን ዳሰሰ፣ደረጀን ተከተለ። ሁሉም አደራጁት፣አሰለጠኑት፣መሩት።

እነዛ መሪዎች ድንቅ ነበሩ፣ያ ህዝብ የእሳት ጎርፍ ነበር።ብልጽግናን ፈጃት፣ሻብያን ለበለባት፣እነባጫ ተራወጡ፣እነ ብርሀኑ ፈረጠጡ፣እነ አበባው ግራ ገባቸው፣እነ አብይ እንቅልፍ ከዳቸው።

ያ በህጸናትና በሴቶች ላይ የግፍ ጽዋ ሲራጭ የከረመና በቂ ዝግጅት ሳይኖር ዘው ብሎ የገባው ወስላታ ሰራዊት መውጫ አጣ፣አብዛኛው ግፍ በሰራበት በዚያው ምድር ፍርዱን በላ፣እዚያው ተቀበረ፣ማዳበሪያ ሆነ፣የታደለው ምርኮኛ ሆኖ የአለማችንን ትልቁን የምርኮኞች ሰልፍ አሳየ።

የዛሬ አመት የካቲትን እንዳያከብር ቢከለከል ቀይና ቢጫ ፊኛ ነፍቶ ወደሰማይ ቢለቅ ደረቱ ላይ ለመተኮስ ቅንጣት ታክል ሀሳብ የማይገባቸው የአብይ አህመድ ወጠምሾች ፊኛውን በጥይት እየመቱ ቢያፈነዱበትም ዘንድሮ በድል ማግስት፣በፈረጠመ ክንድ ታጅቦ በአገርነት ዋዜማ፣ታፍሮና ተከብሮ #የካቲተ_ለካቲትን በብዙ ምርኮ እያከበረ ነው።አብይና ኢሳያስ ግን አሁንም ለህልውናቸው፣ለደህንነታቸው፣ለስልጣን ለወንበራቸው እንቅልፍን እንዳላዩ፣እረፍትም እፍረትም ሳይሰማቸው እንዳሉ አሉ።

እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቼ!!!

ጀግኖች ወንድም እህቶቼ!!!

ትግራይ አሸንፋለች!!!

ኦሮምያም ታሸንፋለች!!!

Read More