INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የአድዋን ድል በአል ለማክበር የሞራል ብቃት ያለው ማነው?

የአድዋ 126ኛ በአል ለማክበር የሚቻለው የአድዋ ተራሮች ባለቤት የሆነው የትራይን ህዝብ በማክበር ነው::

የቆየውን የጀግንነት ታሪክ በአዲስ የጆኖሳይድ ወንጀል ተቀይሯል:: ዛሬ የአድዋ ድል ባለቤት ነኝ የምትለውና በአብይ አሕመድ የምትመራው ኢትዮጵያ በትግራይ ህዝብና በአድዋ ተራሮች ላይ ታሪክ የማይረሳው ወንጀል ተፈፅሟል እየተፈፀመ ነው::

126ኛ አመት የአድዋ ድል በአል ዋናው ባለቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው: ያም ሆኖ የጥቁሮች ታሪክ ነውና በኢትዮጵያም በአሜሪካም ያሉ ጥቁር ህዝቦች ሊዘፍኑለት ሊኮሩበት ይችላሉ: ነገር ግን ራሳቸው ባፈረሱት ታሪክ ላይ ቆመው መሆን የለበትም::

በአፄ ሚኒሊክ ታሪካዊ ስህተት በ1881 አ.ም በውጫሌው ውል ፈርመው ለጣሊያን አሳልፈው የሰጡት የአገር ክብር ለ1888 የአድዋ ጦርነት ሰበብ/መነሻ ነበር::

በሚኒሊክ ሴራ የተፈፀመው ወረራ ገፈት ቀማሽ የሆነው የትግራይ ህዝብ ነበር: የድሉ ባለቤትም በቀደምትነት ህዝቡና የጦር መሪዎቹ እነ የአፍሪካው ጀነራል አሉላ አባነጋ: ራስ መንገሻ: ራስ ስብሃት: ባሻይ አውአሎምና ሌሎች የትግራይ የጦር አርበኞች መሆናቸው የተለያዩ የታሪክ ፀሃፊዎች ከትበውታል::

በዚህ ጦርነት ከሁሉም አከባቢ ለእርዳታ የደረሱ ጀግኖች መኖራቸው ለመካድ አይደለም ነገር ግን ታሪኩና ጀግንነቱ በቤተክርስቲያን ተደብቀው ለነበሩ አንድ የሴራው ጠንሳሽ ንጉስ ተሰጥቶ የትግራይ ህዝብና ጀግና መሪዎች ከታሪክ መዛግብት ለመፋቅና ዋና ባለቤት ለመምሰል የሚደረገው ዘመናዊ ሴራ መኖሩን ለምስታወስ ያህል ነው::

የትግራይን ህዝብ ታሪክ በመስረቅ የሚታወቁት የኢትዮጵያ መሪዎች: የአድዋ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የሃይማኖትና የባህል ቅርሶችም ሳይቀር "የእኛ ብቻ" አባዜ ላሁኑ የጥፋት ዘመን አድርሶናል::

የፅሁፌ መነሻ በታሪክ ለመነታርክ አይደለም: ዛሬ በኢትዮጵያ የአድዋን በአል ለማክበር የሚደረገው ሽርጉድና አዲስ ትርክት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥኖች መስኮት የሰማሁት ስላስቆጣኝ ነው::

ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በደገፈውና በአብይ አሕመድ የሚመራው ህዝብን ከምድረ-ገፅ የማጥፋት (genocidal war) በትግራይ ህዝብና በአድዋ ተራሮች እየተፈፀመ መሆኑን እያወቁ በትግራይ ህዝብ ሬሳና በአድዋ ተራሮች ውድመት ላይ ቆመው ስለ አድዋ ድል ማውራት ምን አይነት ጭካኔ/ድንቁርና ነው: ምንስ አይነት ንቀት ነው::

አባቶቻችን የውጭ ወረራ የመከቱበት የትግራይ መሬት ዛሬ የውጭ ጠላት ጠርተው ካስወረሩ በኃላ በተወረች አድዋ የድል በአል ማክበር ምን ይባላል?

የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያን የጥንትም አዲሱም ታሪክ ለማቆየት መለኪያ የሌለው ከባድ መስዋእትነት እንዳልከፈለ ሁሉ: ዛሬ በጦርነት ማንበርከከ አቅቷቸው በረሃብና በመድሃኒት እጥረት እንዲያልቅ በሚያጨበጭቡለት መሪና እሱ ለጥፋት በጋበዛቸው የኤርትራና የአማራ አመራሮች በ360 ዲግሪ የተከበበችና በሁሉም ግንባር በጦርነት ላይ ያለች ትግራይ የሌለችበት የአድዋ ድል ለማክበር የሚችል ሃይል ሊኖር አይችልም::

በትግራይ ህዝብ ላይ ክህደት የፈፀመ ሁሉ እንኳን በትግራይ ተራሮች ስም ሊነግድ ይቅርና ገና በታሪክ ይጠየቃል: በውሽት የተመሰረተ የአዲስ አበባ ስርአት ለጊዜው የውሸት ካባ ለብሶ ሊሸልል ይችላል: እውነቱ ግና እያደረ ይገለፃል::

የትግራይን ህዝብ የገደሉት: የደፈርት: ሃብቱን የዘረፉትና ቅርሱን የሰረቁትና: በውንጀሉ ተባባሪ የሆኑት ሁሉ : ደፍረው ሲመጡ በትግራይ መሬት የጣሊያን ወራሪ ሰራዊት እጣ ፈንታ አግኝቷል የቀሩትም የትግራይ ተራሮች መቀበሪያቸው ይሆናል::

ይብላኝ ለከሃዲዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ ሺዎች አሉላዎች አፍርተዋል፤ በአሉላ ዘመቻ የተጀመረው የመከላከል ዘመቻም ደብረብርሃን ደረስ እንዴት እንደተንደረደረ ታይተዋል። ስለዚህ የአድዋ ድል ለማክበር የሞራል የበላይነት ያለው የአድዋ ተራሮች ባለቤት የትግራይ ህዝብ ነው። የተሰረቀው ታሪካችን፤ የተመዘበረው ቅርሳችን እስኪመለስና ትግራይ ይህንን የክፋት ዘመን በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።

ትግራይ ትስዕር!

Read More