INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

ወልቃይት_የኣማራ_ፖለቲካ_ግብኣተ_መሬት (#መቃብር) ናት፡-

(በተፈጠረ ሁኔታ ኣስገዳጅነት የትግራይ ሃቅ ማቅረብና የተፈበረከ እና የተዛባ ትርክት በታሪካዊ ማስረጃዎች ማፍረስ ስለ ነበረብኝ ነው ባለፈው ጊዜ በኣማርኛ ከትቤ ለመዘርጋት/ለማጋራት ወደ ማህበራዊ ሚድያ እመለሳለሁ ብየ ካቀድኩት ቀድሜ ብቅ ያልኩት፡፡ ያንን በመታዘብ ወደ ማህበራዊ ሚድያ ጠቅልየ የተመለስኩ የመሰላችሁ ገና ኣልመጣሁም ነው መልሴ፡፡ የተጣበበ ጊዜየን እየተጋፋሁ ኣልፎ ኣልፎ በትግርኛ ከትቤ የምለጥፈው፤ የትግራይ ፖለቲካ ከውስጥ ወደ ውጪ ነው ማነጣጠር ያለበት የሚለውን ኣዲሱ ኣቋሜን መሰረት በማድረግ በትግራይ የፖለቲካ ምህዳር የለውጥ እርሾ ለመጠንሰስ እና የማይቆራረጥ የለውጥ ሂደት ለመፍጠር ያለመ ውስን ተሳትፎ እንጂ እርሱም ቢሆን ወደ ማህበራዊ ሚድያ መመለሴን ኣያመላክትም፡፡ የመመለሻየ ቁርጥ ያለ ቀን ማስቀመጥ ባልችልም በኣዲስ ቅድ እንደምመለስ ግን ማሳወቅ እችላለሁ፡፡ )

ባለፈው ከትቤ ባጋራሁት (በዘረጋሁት) ጉዳይ በታሪካዊ እና ኣስተዳዳራዊ ታሪክ ሃቆች የሚሞግተኝ ባይገኝም (በባዶ ከመፎከር ኣልፎ የኔን ሃቅ በማስረጃ ኣስደግፎ መሞገትም ኣይቻልም፡፡ የኔን ማስረጃ የሚቃረን ማግኘት ስለማይቻል/ስለሌለ) #በጊዚያዊ_የሃይል_ሚዛን_የተፈጠረው_የመሬት_ወረራ ዘላቂ ይሆናል ብለው በመኮፈስ ትምክህታቸውን ያንፀባረቁብኝ ጥቂት የኣማራ ብሄርተኞች ስለ ነበሩ ፈስ ለባለቤቱ ኣይሸትምና (በጥላቻ፣ በፍርሃትና በእብሪት የታወረ ኣውድና ኣዝማሚያ በትክክል ሊያነብ ኣይችልምና) #ኣንድ_እግር ተመልሼበት ሌላ ተጨማሪ የወልቃይት ገፅታ ለማሳየት ወሰንኩ፡፡

ኣራት ኣመት ገደማ ሊሆነው ይችላል ኣንድ ወዳጄ ለነበረ የኣማራ (ሸዋ) ተወላጅ ለምንድን ነው የኣስተዳደራዊ ታሪክ፣ የህዝብ ስብጥር (Demography) እና የህግ ድጋፍ ሳይኖራችሁ የወልቃይት ጉዳይን እያጎላችሁ በኣማራ እና በትግራይ መካከል የማይሽር ጠባሳ የምትፈጥሩት? የሚል ጥያቄ ስሰነዝርለት፤ ‹‹ #የወያኔ_ስስ_ብልት ወልቃይት ላይ ነው ያለው›› የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ እንግዲህ እውነት ባይኖረንም ህወሓትን ለመምታ ወልቃይት ህዝብ ለኣመፅ ለማነሳሳት (Mobilizing Factor) እንጠቀምበታለን መሆኑ ነው፡፡ ከመሬት ወረራ ኣልፎ በትግራይ እና በተጋሩ (ትግራዮች) ጉዳት የደረሰ እና እየደረሰ ያለ ቢሆንም፣ ወልቃይት እንደ ስስ ብልት ለመጠቀም የወሰነ ሃይል እንዴት ፖለቲካውን ወደ መቃብር እንደከተተችው ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ከዛ ኣልፎም የኣማራ ፖለቲከኞች ባራመዱት የጥላቻ እና የሰው ልጅ ፍጅ (ማንነት መሰረት ያደረገ ጥቃት ይለዋል ብልፅግና) ፖለቲካ ወልቃይት የፌዴሬሽኑ ሞት ሰበብ እየሆነች ነው የሚል ብልፅግና ድርድር እንዲያስብ ካበቁት ኣንዱ ምክንያት ኣድርጎ ኣቀርቧል፡፡

ለንፅፅር እንዲመች ሃሳቤን ቅድመ እና ድህረ ወልቃይት የኣማራ ፖለቲካ በሚል በሁለት ከፍየ ኣቅርቤዋለሁ፡፡

ሀ. ቅድመ-ወልቃይት የኣማራ ፖለቲካ

1. በኢትዮጵያ ኣንድነት ተቆርቋሪነት የፖለቲካ የሞራል ልእልና የተጎናፀፈ
2. ፖለቲካዊ ኣተሳሰቡ ልእል ብሄር ወይም ሃገራዊ ብሄርተኝነት የሚያራምድ እንድሆነ ተደርጎ የሚወሰድ
3. በኢትዮጵያዊነት እና በኣንድነት ስም ከኣማራ ብሄር ተወላጆች ኣጥር ኣልፎ ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች እና ህዝቦች ማንቀሳቀስ፣ ማደራጀት የሚችል
4. ፖለቲከኞቹ ኣንደበተ ርትኡ፣ ጥልቅ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እውቀት የጨበጡ (sophisticated) ተደርገው የሚቆጠሩ
5. የነቁ፣ ዘመናዊ እና የተገራ ኣንደበት ያላቸው ተደርገው የሚወሰዱ፡፡ የቀኝ ክንፍ ፖለቲካ ኣራማጆች እንጂ ኣማራ ብሎ ለመጥራት ሰው የሚከብደው፡፡
6. ራሳቸውን ስልጡን ኣርገው (ከትግራይ የተዋስዋቸውን ፊደል፣ እምነትና ቤተ መንግስት እየመነዘሩ) ከመቁጠራቸው የተነሰ ጦብያውያን ተምረው ኣማራ መሆን ነው የሚመኙት እስከ ማለት የደረሱ፡፡
7. ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የኣገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው የመስራት፣ የመኖርና ሃፍት የማፍራት ዜግነታዊ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው የሚታገሉ
8. ያለ ልዩነት ለኢትዮጵያውያ በሙሉ የሚቆረቆሩ እና ሰብኣዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች እንዲከበሩ ኣብዝተው የሚጮሁና የሚተጉ እና ህዝቦች ከቀያቸው መፈናቀል የሚቃወሙ
9. የብሄር ፖለቲካ ለኣንድነት ጠንቅ ነው በማለት የሚኮንኑ
10. ቋንቋ እና የህዝብ ኣሰፋፈር መሰረት ያደረገ ክልላዊ ኣስተዳዳረዊ ኣደረጃጀት የሚቃወሙ
11. መሬት (ግዛት) የሁሉም ኢትዮጵያውያን ይዞታ እንጂ የቡድን ርስት መሆን የለበትም ብለው የሚቃወሙ

ለ. ድህረ-ወልቃይት የኣማራ ፖለቲካ

1. የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ ካባ (ጭምብል) ወልቆ በኣማራ ፖለቲካ ዛቢያ ብቻ የሚሽከረከሩ
2. በኢትዮጵያ ስም ፖለቲካ ሲያራምድ የነበረ የኣማራ ፖለቲከኛ ሁሉ የኣማራ ግዛት ኣስፋፊነት የተዘፈቀበትና ጭምብሉ ወልቆ የነጋበት ። የኣማራ ግዛት በወረራ ለማስፋፋት ኢትዮጵያን ያጡበት: የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከእጃቸው የወጣበት።
3. ከብሄር በታችም ወርደው የጎጥ ፖለቲካ የሚያራምዱ እና የተዘፈቁ
4. የጥላቻ እና የሰው ልጅ ፍጅት ፖለቲካ ኣራማጅ፣ ሰባኪ እና ተግባሪ፡፡ የቤተ ክህነት ሰዎች ሳይቀሩ የጥላቻ እና የሰው ልጅ ፍጅት ሰባኪ የሆኑበት፡፡ ከዛም ኣልፈው ጦር ግንባር ላይ ተገኝነተው የግዛት ማስፋፋት ዘመቻ የባረኩበትና ያበረታቱበት
5. ህዝብ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ የሚገድሉ እና ማንነት ለማጥፋት የሚተጉ
6. በደም ጥራት የሚያምኑ እና የኣማራ ፖለቲካ በአባትም በእናትም ከኣማራ ብቻ የሚወለዱ የሚሰባሰቡበት፣ ከኣማራ ውጪ የትውልድ ሃረግ የቀላቀለ ከስብስቡ የሚወገድበት ፖለቲካ የሚያራምዱ
7. ፖለቲካቸው እና ፕሮፓጋንዳቸው ኋላቀርና መንጋዊ (Barbaric & Herd) ከመሆኑ የተነሳ የሌላ ብሄር ተወላጅ ወጣቶች የሚሳለቁበት (Mood የሚይዙበት) ወደ መሆን የወረደ፡፡ የሌላ ብሄር ተወላጆች የኣማራ ፖለቲከኞችና ወጣቶች ያልነቁ፣ ኣንደበታቸው ያልተገራ እና ኋለቀር ኣድርገው የሚቆጥሩበት ደረጃ የደረሰ፡፡
8. ተበድልን ብለው በእምነት ይሁን በብሄር ስም ቢጮሁ ማንም ቀልብ የማይሰጣቸው፡፡
9. የእምነትና የሃይማኖት ተጋሪዎቻቸው ሳይቀሩ ጭሆታቸውን የማይጋሯቸው ደረጃ የደረሱ፡፡ በእምነት ስም ኣብሯቸው መሰለፍ ይቅርና ኣብሯቸው ለማምለክ ፍላጎት የጠፋበት ደረጃ የደረሱ፡፡
10. በባንዲራ ስም ለማደራጀት ቢጥሩ እና በደል ቢያስተጋቡ ታሪክና ውክልና የሚጋራቸው ኣጥተው ጭራሮ ሆነው የቀሩ፡፡ ሌሎች ብሄሮችን ከጎናቸው ማሰለፍ ያቃታቸው፡፡ ከዚህ ይልቅ የኣፀፋ ተቃውሞ እና እርምጃ የሚጋብዙበት ደረጃ የደረሱ፡፡
11. መግደል፣ ማፈናቀል፣ ማፅዳት፣ መፍጀት፣ ንብረት መዝረፍ ቅቡል ስላደረጉት ኣማራ ሞተ፣ ተፈናቀለ፣ ንብረቱ ወደመ ብሎ ቢጮሁ የሚሳለቅባቸው ካልሆነ ጭሆታቸው የሚያስተጋባላቸው የጠፋበት፡፡ ኣላቃሽ እንኳን ያጡ ፡፡
12. በኣንድነት ፖለቲካ ስም በኣማራ የፖለቲካ ጎራ ተሰባስበው የነበሩ ከኣማራ ፖለቲካ ለመውጣት የሚፍጨረጨሩበት፡፡ ለኣብነት፡- ኤርሚያስ ለገሰ ዋግጅራ የመሳሰሉ የኣማራ ፖለቲካ ቀላዋጭ የሆኑት የወልቃይት የፖለቲካ ማእክልነት ሲሰብኩና ሲያጋግሉ እና ኦሮሞ ጠል የሆነ የከተማ ጎጠኝነት ፖለቲካ ሲያራምዱ ኖረው፣ የኣማራ ፖለቲካ ወልቃይ ላይ መሞቱ ሲገለፅላቸው ከኣማራ ፖለቲካ ለመውጣት ሲጣጣሩ መታዘብ ይቻላል (ኣማራ ነክ በሆኑ ውይይቶች ባለመገኘት እና ጥያቄ ሲነሱበት በዘዴ በመሸሽ የሚገለፅ exit ማመቻቸት የሚደረግ ጥረት መታዘብ ይቻላል፡፡ ሁሉም ነገር ለህግዴፍ ኣሸክመው የኣማራን ፖለቲካ ለመታደግ ከሚጥሩ እና ፖለቲካዊ ይዘታቸው ኣሃዳዊ ቢሆንም በወልቃይት ፖለቲካ ያልወደቁት በእነ ልደቱ እንዴት እንሚቀና እና ጠጋ ጠጋ እንደሚል መታዘብ ይቻላል፡፡
13. ለፖለቲካ ኣላማው የሚያነሳሳቸው ሃይል እንጂ የኣማራ ፖለቲከኞች ከኣማራ ውጪ የሚያነሳሱትና ከጎናቸው የሚያሰልፉት ሃይል ማግኘት የማይችሉበት ደረጃ የደረሱበት
14. የኣማራ ፖለቲከኞች የፌዴራል ተቋማት ለተቆጣጠረ ሃይል (በዋነኝነት ኦህዴድ) ኣድረው ፍላጎታቸውን ለማሟላትና ተቀናቃኞቻቸው ላይ ጉዳት ለማድረስ ከመጣር በስተቀር ሌላ ኣማራጭ የሌላቸው፡፡
15. የኣማራ ፖለቲካ የሚፀየፍ እንጂ ኣብሮ ለመታገልና የፖለቲካ ሽርክና ለመፍጠር ፈላጊ የሌለው፡፡ ከህወሓት እና ህወሓት የጠፈጠፈቻቸው ድርጅቶች የፈጠሩት ብልፅግና በስተቀር ማንም ሃይል እንዲቧደናቸው የማይፈልግ፡፡ ማንኛውም የተቃውሞ ጎራ ከኣማራ ፖለቲከኞች ጋር ለመጣመር ፍላጎት የሌለው፡፡
16. የኣማራ ፖለቲካ ሃይሎች የፌዴራል ተቋማት ከተቆጣጠረው ሃይል ጋር ቢኳረፉ ኣውላላ ሜዳ ላይ ተሰጥተው መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆኑ የዘለለ ተፅእኖ መፍጠር የማይችልበት ደረጃ መድረሱን የተጋለጠበት ፡፡ ጭሆቱን በጭሆት ለማፈን የሚሞክሩ እንጂ የሚያስተጋቡለት ሃይሎች የሌለው ጭራሮ የሆነበት፡፡ የፌዴራል ተቋማት የተቆጣጠረው ሃይል ላይ ፍላጎታቸውን ኣላሟላም ወይ ተጋፋን ብለው ቢያጉረመርሙ ተጨማሪ ውርዴት እና ኪሳራ ከማስከተል በስተቀር ተፅእኖ ማሳደር የማይችሉ፡፡
17. የዜግነት ፖለቲካ ኣራማጅ ነን ባዮች ሁሉ ጭምብላቸው ተገልጦ ከወጡበት ኢትዮጵያዊነት ማማ የፈጠፈጡበት፣ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ኣንድነት ስም ፖለቲካ ማራመድ የማይችሉበት ደረጃ የደረሱበት፣ ፖለቲካዊ ህይወታቸው ያበቃበት፡፡ ከፖለቲካ ኣልፎም ክህነታዊ ማእረጋቸው የቀለለበት: ክብር ያጣበት፡፡
18. የፌዴራል ተቋማት የተቆጣጠረ ሃይል ድጋፍ ካልታከለበት ጉዳያቸውን በራሳቸው ኣቅምና ኣደረጃጀት ማስፈፀም የማይችሉ የእንቧይ ካብ የሆኑበት፡፡ እድል ቢያገኙ የኣማራ ክልል ተቀራምተው የተለያዩ ክልሎች ለመፍጠር ሊቀራመቱት ያሰፈሰፉበት፣ የኣማራ ክልል The Sick Man of the Federation የሆነበት፡፡

Read More