INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኣንጋፋው ኣምባሳደር ስዩም መስፍን ከBBC

የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኣንጋፋው ኣምባሳደር ስዩም መስፍን ከBBC ትግርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወሳኝ ነጥቦችን ኣንስተዋል፡፡ ወደ ትግርኛ ተተርጉሞ ባጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ እንዲፈታ የእርቅና የሰላም ረቂቅ ሓሳብ የቀረበው የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ ኣቶ #ጌታቸው_ኣሰፋ ፥ የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ሳሞራ_የኑስ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ቴድሮስ_ኣድሓኖም ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ኣብዪ ኣሕመድ ምንም የጨመረው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን የእነርሱ ጥያቄና ጥረት ኣብዪ ኣሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጣ የኤርትራው መንግስት ለሌላ ያልረባና እማያዛልቅ ፖለቲካ ተጠቅሞበታል። የተፈለገው የሁሉም የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ወደ ቀድሞው ሁኔታ መቀራረብእንጂ በኣብዪ ኣሕመድና በኢሳያስ ኣፈወርቂ ብቻ እንዲወሰን ኣልነበረም።

ከነ ውስንነቱ ጋር ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ኣመርቂ የሆነ የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ተካሄዷል። ለኣውሮፓውያንና ኣሜሪካውያን ከ300 - 400 ዓመታት የፈጀባቸው የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ እኛ በሁለት ኣስርት ዓመታት ውስጥ በምንችለው ሁሉ ሰርተንበታል ፤ ይህም ምን ግዜም እምንኮራበት እንጂ እምንቆጭበት ሁኔታ የለም፡፡

በልማት ኣንፃር ሲታይ ኢህኣዴግ ኢትዮጵያን ሲረከብ ድሃ ከሚባሉ የኣፍሪካ ኣገራት ከታች 8ኛ ነበረች፡፡ ነገር ግን በተለይ ባለፉት 15 ዓመታት ለተከታታይ ባስመዘገበችው ባለ 2 ድጅት እድገት በኣፍሪካ ኣህጉር ከሚገኙ ከፍተኛ ሃብትና እድገት ካስመዘገቡ 6 ኣገራት ተርታ እንድትሰለፍ ችላ ነበር።

▲ህወሓት ከሚያስተዳድረው የገዛ ክልሉ ውጪ በሌሎች ክልሎች ሄዶ ኣልመራም፡፡ በኣማራ ክልል ሲመራ የነበረው ብኣዴን ነው ፤ ደቡብ ደህኢህዴን ነው ፤ ኦሮሚያም ቢሆን ኦህዴድ ነው ሲመራ የነበረው፡፡ ኣንድ የኦህዴድ ኃላፊ ሳይፈርምበትና ሳያውቀው ኣንድ ስኩየር ሜትር መሬት ለምንም ስራ ኣኣልዋለም ፥ የትም ኣልሄደም፡፡ በሚያስተዳድሩት ክልል ዘረፋ ይፈፀም ከነበረ ዘራፊዎቹ እነርሱ ራሳቸው ናቸው ፤ ጥፍር የሚነቅል የፀጥታ ኃይል ከነበራቸው ተጠያቂዎቹ እነሱ ራሳቸው ናቸው፡፡ በማንኛውም ክልል ትግርኛ የሚናገር ኣስተዳዳሪ ኣልነበረም፡፡ ስለዚህ እነሱ ለስልጣን ሲሉ ህወሓትንና የትግራይን ህዝብ ብቻ ኣይደለም የካዱት ፤ እንወክለዋለን የሚሉትንም ህዝብ ጭምር ስም እየቀያየሩ ባደባባይ ክደዋል፡፡

▲እውነት እነርሱ ህወሓትን እንደሚወነጅሉትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ እንደተሰማሩት ከህነ በኢትዮጵያ ገለልተኛ የሆኑ ኣጣሪዎች እንዲሁም በዓለም ላይ የተመዘበረን ገንዘብ መርመረው የሚያወጡ ተቋማት መጥተው ይመርምሩ፡፡ ወደ ውጭ የሸሸ ገንዘብ ካለ ፥ እያንዳንዳችን በኣካውንታችን ያካበትነው ካለ ፥ የወሰድነው መሬት ካለ ይጠና ፤ ይመርመር። ከዚያም የኢትዮጵያ ህዝብ የገንዘብና የመሬት ቀማኛው ማን እንደሆነ ይወቀው።

▲ኣብዪ ኣሕመድ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ከናይል ተፋሰስ ሀገራት፣ፈ ፥ በተለይም ከሱዳንና ከግብፅ ጋር ተጀምሮ የነበረውን ውይይት ትቶ ነው የIGADና የኣፍሪካ ህብረትን በመናቅ ግብፅን ይዞ በቀጥታ ወደ ኣሜሪካ የሄደው። ሱዳኖችን ወደ ኣሜሪካ ሄጃለሁም ብሎ ኣልነገራቸውም ፤ ሱዳኖች ወደ ዋሽንግተን ተጠርተው ነው የሄዱት፡፡ ይሄ ከኣጎራባችና ከኣህጉራዊው የቀጠናችን የስትራቴጂክ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ኣኳያ እጅግ በጣም ኣሳፋሪና ታሪካዊ ስህተት ነው። የኣባይ ወንዝ ኣፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። አኣብዪ ኣሕመድ ህዳሴ ግድብን ለባለ ጠጎች ሸጦታል ፤ ነገ በኣገር ክህደት ይጠየቃል፡፡

▲ኢሳያስ ኣፈወርቂ ‘"...የድበር ጉዳይ አያሳስበኝም ፤ የሚያሳስበኝ ህወሓትን ማጥፋት ነው ፤ የህወሓትን ኣስተሳሰብ ማጠብ ነው...'’ ብሏል፡፡ ኣጥቦ እስኪጨርስ እንጠብቀዋለን ፤ መቼ እንደሚያጥብና እንደሚያጠፋ የኤርትራ ህዝብ ይጠይቀው፡፡ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ግን ኢሳያስ በህወሓት ፥ በትግራይ ህዝብም ሆነ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቅንጣት ታክል የሚያመጣው ለውጥ የለም። ከምኞት በቀር ኣቅሙም እውቀቱም የለውም።

▲የኣብዪ ኣሕመድ '‘Role model’' ኢሳያስ ኣፈወርቂ ነው፡፡ ‘'IGADን ኣፍርሰው’' ብሎ ኣዝዞት ኣብዪ ኣሕድ IGADን ኣፍርሶታል ፤ ኣብዪ ኣሕመድ ነው የIGAD ሊቀመንበር የነበረው፡፡ ኣሁን IGAD የት ኣለ? IGAD ቆዳው ብቻ ነው የቀረው፡፡

▲ኣሁን በስልጣን ኮርቻ ላይ ያለው ቡድን ህጋዊነት ተላብሶ ስልጣን ላይ የተቀመጠ ኣይደለም፡፡ ነገር ግን እስኪ እንታገሰው ብለን ቆይተናል፡፡ ነገር ግን ከመስከረም 25 በኋላ በስልጣን ላይ ሊያቆየው የሚችል ምንም ኣይነት ህጋዊና ህገ-መንግስታዊ መሰረት የለውም፡፡ ከዛ በኋላ ሃገሪቱ ውስጥ የሚከሰተው ስርአት ኣልበኝነት ነው፡፡ ይሄ ህወሓት ወይም የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶችና ብሄር ብሄረሰቦች እያነሱት ያለው ስጋት ነው፡፡

▲ኣሁን ያለው የመፍትሄ አማራጭ ቡድኑ ጉዳዩን በጥሞና ኣይቶ ፥ በኃይል እንደማይቀጥል ተገንዝቦ ሁሉንም የሀገሪቱ ህጋዊ ስብእና ያላቸው ፓርቲዎች የተሳተፉበት መፍትሄ እንዲመጣ ፈቃደኛ መሆን ኣለበት፡፡ ነገር ግን በኃይል እገዛለሁ ካለ እንኳን የኣብዪ ኣሕመድ ሰራዊት የደርግ ሰራዊትም ባለበት መቀጠል ኣልቻለም፡፡

▲ኮሮና ለኣብዪ ኣሕመድ ከሰማይ የወረደለት መና ነው፡፡ ኮሮና ከመምጣቱ በፊትምኮ ምርጫው በነሓሴ ወር እንዲካሄድ ነው የፈለገው፡፡ በዝናብ ወቅት እንዲካሄድ የወሰነው ምክንያት ይፈልግ ስለነበረ ነው፡፡

▲የትግራይ ህዝብ ምርጫ ማካሄድ እችላለሁ ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደሰትበት ይገባ ነበር ፤ ኣብዪ ኣሕመድም ቢሆን እልል ማለት ነበረበት፡፡ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ስለሆነች ብቻ ከሌሎች ጋር ተጠፍረህ ሂድ ይባላል እንዴ? ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም እናካሄዳለን ካሉ እንደግፋቸው ነው ማለት የነበረበት፡፡ ከኣፍንጫው ኣርቆ ማየት ቢችል ኖሮ በምርጫው በተደሰተ ነበር፡፡ በተከበረው ፓርላማ ቃለማሃላ ሲገባ "...ህገ-መንግስትን ኣክብሬ እሄዳለሁ..." ብሎ ህገ-መንግስቱን የሰጠውን ኃላፊነት ለህዝብ ኣስረክባለሁ ስላለ ጦርነት ሊያውጅ ነው 6!? ህገ-መንግስቱን ያፈረሰና ህገ-መንግስቱ ከሰጠው በላይ ስልጣኑን ለዓመታት ያራዘመ ያልተቀጣና ያልተገረፈ ፥ ጦርነት ያልታወጀበት ፥ ህግን ኣክብሮ በሚሄደው ላይ ጦርነት ሊያውጅ ነው !? እናየዋለን !!! በመጨረሻ ወዴት እንደሚሄድ ጊዜ ያሳየናል፡፡

[የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኣንጋፋው ኣምባሳደር ስዩም መስፍን]