ሲኦልን የሚጠብቅ መልኣክ
Source: https://www.facebook.com/103795992190808/posts/126058239964583/
በ kaleab belay Nega (1 march 2022)
ትግራዋይ በትግራዋይነቱ ብቻ በዚች ከተማ በታሪክ ይቅር የማይባል ማለቅያ የሌለው ግፍና በደል ተፈፅሞበታል ። ያለፈውን ለታሪክ ይቆይልን እና ከህዳር 18-የካቲት 07 በመናኙ ስም የተሰየመውን የምድር ሲኦል በግርድፉ ላስቃኛቹ ።
ትግራዋይ ብቻ ለማሰር እና ለማንገላታት ፣ ለማስራብ በረሃብና በሽታ እንዲሞት ከሞት ቢያመልጥ እንኳ የማይድን በሽታ ይዞ እንዲወጣ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዎጅ ተከትሎ ባባ ሳሙኤል እስር ቤት የታሰረው 5000 የሚሆን ትግራይ ተወላጅ ትግራዋይ በመሆኑ በየቀኑ የሚገረፍ ምግብ ሳሙና ተከልክሎ እንዲራብና በበሽታና በምግብ ጠኔ እንዲያዝ ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት መሆኑ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው ።
ከኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ( ማእከላዊ) ወደ ኣባ ሳሙኤል እስር ቤት ስንወሰድ ምንም እንደማያስፈልገን ሁሉም ነገር የምንሄድበት ቦታ እንደሚሰጠን ተነገረን ።
ፍራሻችን እንኳ እንዳንይዝ ከተደረገ በኃላ ኣባ ሳሙኤል የተቀበለን ግን የተገላቢጦሽ ሆነ ። ባባ ሳሙኤል በቀን ሁለት ዳቦ እየበላን .. ያለ በቂ ምክንያት ሰው እየተገረፈን እና ኮንክሪት መሬት ላይ እንድንተኛ ተደረገ ።
ከገባን በኋላ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) አባላት ናቸው ሙርከኛ ናቸው ስለተባልን እኛም እስክንፈታ ድረስ ....
'ታጋይ ምግብ አይመረጥም ፤ ታጋይ መኝታ አይመርጥም"' ሆነ መፈክራችን።
በዚህ ሁሉ ችግር በየቀኑ በተልካሻ ምክንያት የሚገረፈው ሰው ሳይበቃቸው በየሳምንቱ እሁድ ቱታውን እየለበሰ ለመግረፋ የሚመጣ ገርፎም የማይጠግብ ....እናንተ ብቻ ናቹ እንዴ ጀግኖች? እኛም ጀግና አለን ! "አንድ ትእዛዝ ነው ምጠብቀው እረሽናቹዋሎ" እያለ የሚያስፈራራ ኣለቃ የቤዛ ዱላ ክፋት ጥግ አንረሳውም ።
በዚህ መሃል በተልካሻ ምክንያት ሰው ሲገረፍ እንደነ ቤዛ አይነት ሰዎች ብዙዎች ቢሆኑም ፤ እጃቸውን ያልጨመሩ ይባስ ብለው ሃዘናቸው በእንባ የገለፁ አሉ ። ከነዚህ የሰው ደጋጎች ያንበሳ ድርሻ የሚወስደው ግን የፌደራሎቹ መሪ ጉተማ ሳዶ ብሉዶ ነው ።
ጉተማ ሳዶ ብሉዶ ሲበዛ በፍትሕ የሚያምን ፤ ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባው ያለ ምክንያት ሰው መመታት የለበትም ብሎ የሚከራከር ፤ ሰው በቋንቋ እንጂ በዱላ እንደማይግባባ የገባው ሲኦልን የሚጠብቅ የአባ ገዳ ልጅ መልእክ ነው ።
ጉተማ እዛ ባይኖር ንሮ በዱላ አካሉ ጎድሎ የሚወጣ ብቻ ሳይሆን ሂወቱን አጥቶ የሚወጣ ይኖር ነበር ፤ የጉተማ መልካምነት አባ ሳሙኤል የነበሩት ሌሎች የሚጨምሩበት ቢሆንም ኣንድ ነገር ልንገራቹ ።
ጉተማ ማንም ሰው እንዳይመታ አጥፍቶ የሚቀጣ ቢኖር እንኳን ከአንድ ወታደር በላይ እንዳይቀጣው ። ሲቀጣው እስፖርት እንዲያሰራው ሲናገር እስረኛው ለሱ ድጋፍ በመስጠት እናመሰግናለን አለው ። በአላህ ምግብ የማይበሉ በምግብ እጦት የሚሰቃዩ ሰዎች መምታት ለምን ብሎ የሚከራከር ሰው አትምቱ እስረኛ በህግና በህግ መያዝ አለበት የሚል ካየኋቸው የዘመኑ ጀግና ነው።
ወደ ግቢ ፖሊስ ሲገባ እስረኛው ከዱላ ለማምለጥ ይበተናል አንድ ቀን ጉተማ ከጓደኞቹ ወደ ግቢ ሲገባ እስረኛው መበተን ጀመረ ጉተማ አረ በአላህ ቁጭ በሉ ይሄን ያህል አውሬ አታርጉን ብሎ ሰዉ በያለበት እንዲሆን ፈገግታ ተሞልቶ ተናገረ ሰውም አምኖት ተቀመጠ ከዛ ቀን በኋላ በትንሹ ያለ ምክንያት የቤዛ ዱላ ስራዋን አቆመች ።
አንድ ሰው ከእስር ሲለቀቅ ቆሽታቸው የሚቃጠሉ ቢነሩም ጉተማ ግን እንኳን ሰው ለማስፈታት ከመጀመርያው ጀምሮ እስረኞች አደላቹሁም የሰራቹሁት ወንጀል የለም የሚል .. ሰው ሲፈታ እጅግ በጣም ደስ ከሚላቸው ግንባር ቀደሙ ሰው ነው ።
ከሚዛን ቴፒ የመጡ እስትንፋሳቸው ያልወጣ በረሃብ ውሃ እንኳን መዋጥ የከበዳቸው ተጋሩ እስረኞች ተቀላቀሉ። ያኔ ግቢውን በድንጋጤ ሲዋጥ የነበሩ ያየኋቸው ሴት የፌደራል ፖሊስ አባላት ገነት ፣ማርሸት፣ ቢፍቱ ....ባዩት ነገር ሃዘናቸው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ትዝ ይለኛል ።
የጉተማ ግን ይለያል ለግሉኮስ መትከያ አምስት ቦታ በመርፌ ተፈልጎለት ቦታ የታጣለት እስረኛ ከዞን አንድ ወደ ዞን 2 ጠረጴዛ ላይ እንዲተኛ ውሰዱት ተባለ። ጉተማ በጀርባው አዝሎት መጓዝ ሲጀምር ድንገት የታዘለው ልጅ ለጉተማ በቦሚት ሰውነቱን አጠበው ጉተማ አልተሳቀቀም ይባስ ብሎ ለእስረኛው አይዞህ አትሳቀቅ ይሻልሃል እኔ ልብስ ብቀይር ነው ፈጣሪ አለ ይሻልሃል ብሎ ህክምና እንዲያገኝ አደረገ። የቀረውን አባ ሳሙኤል እስርቤት የነበራቹ ጨምሩበት.....
ጉተማ ሰው በለሌበት ቦታ ሰው ሁነህ የተገኘህ ስቃያችንን የተጋራህ ፤ ገመናችንን በእጅህ የጠረግክ እና የተቀበልክ ነህና በነበረው እስረኛ ስም እጅግ እናመሰግናለን ፈጣሪ ቀሪ ዘመንህ ይባርክ ።
በተጨማሪ የነበረውን ግፍ እና በደል በሶሻል ሚዲያ እና በተለያዩ ዘዴዎች ድምፅ ለሆናቹ ፤ ምግብ ፣ ልብስ ፣ ሳሙና ወደ እስርቤት አምጥታቹ እስረኛውን ያበላቹ ያለበሳቹ ተጋሩ ፣ የኦሮሞ ኣባቶች እና እናቶች ፣ ወጣቶች ከእስረኛው ጎን ለነበራቹ ሁሉ እጅ እንነሳለን ።
Read More
|