ለወንዝ እንጂ ለህዝብ የማትሆን አገር እንድገና መሰራት አለባት:
Source :https://www.facebook.com/100033334580627/posts/651147539339726/
የህዳሴ ግድብ ከጠ/ሚር መለስ ዜናዊና. ኢንጅኔር ስመኝው ውጭ ማሰብ አይቻልም!
ዛሬ የትግራይ ህዝብ በጦርነት ማሸነፍ አቅቷቸው ህዝቡን በረሃብ እንዲያልቅ ከውጭ ወራሪዎች ጋር አብረው የዘጉት "ኢትዮጵያዊያን " መሪዎችና ተከታዮቻቸው : የአባይን ግድብ (ህዳሴ ግደብ) ስራ ጀመረ ብለው ሲቦርቁ ማየት ምንኛ ያተዛዝባል?
ትላንት ለግድቡ መዋጮ ሲጠየቅ በዳያስፖራ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች 80 ከመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ሲያዋጡ "አባይ አይገደብም: ለፖለቲካ ንግድ ነው" እያሉ በየአደባባዩ ሲቃወሙ የነበሩ የጥፋትና ኋላቀርነት አጃቢዎች (short memories ) ዛሬ አገሪቱ በየመአዝኑ እየታመሰችና ህዝቦቿ በጦርነትና በረሃብ እያለቁ አጀንዳ ማስቀየርያ ፈጥረው ህዝቡን ሲያጃጅሉት ማየት እንዴት ያሳዝናል!
የህዳሴ ግድብም ሆነ ቀደም ብለው የተሰሩት ግልገል ግቤዎች ለኢትዮጵያ ህዝቦች የኢኮኖሚ እድገት አጋዥ እንዲሆኑና የትራንስፎርመሽኑ አንድ የሃይል ምንጭ ዘርፍ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም:: አገርና ህዝብ ከፈረሰ ወንዙም ጅረቱ እንድድሮው ለቅረርቶና ሽለላ እንጂ ግድብ በራሱ አገር አያድንም::
የአባይ ተፋስስ አገራትን አግባብቶ የግብፅና የሱዳንን ብቸኛ ተጠቃሚነት በዲፕሎማሲ ያሽነፈውና "አባይን የደፈረ" ብለው የዘፈኑለት: ለህዝቡ መስዋእት የከፈለው መለስ ዜናዊን የከዳች አገርና ህዝብ መሃል መኖር እንዴት ያሳፍራል!
የታሪኬ መሰረት ትግራይ ነው እያለ በአደባባይ የሚፎክር ነገር ግን የታገለለትን ህዝብ እንዲጠፋ የፈረደ : ባለውለታውን "ጁንታ" ብሎ ጦርነት በከፈተ አገርና ህዝብ መሃል መፈጠር ምንኛ ያስጠላል!
አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጆኖሳይድ ለመሽፋፈን በአማራና በአፋር ክልሎች ብቻ ጥቃት እንደተፈፀመ በማስመሰል ከትግራይ ጋር ለማመሳሰል የሚሰራው የውሸት ድራማ እንደ ትላንትናው የራሱ ሴራ መሆኑ ይጋለጣል:: ያኔ የተሰራው ሃጥያት በህዳሴ ግድብ ውኃ ታጥቦ የሚጠራ አይደለም::
የመለስ ዜናዊና ኢንጅነር ስመኘው አሻራ ለጊዜው ከአደባባይ ለማጥፋት ቢሞከርም ዞሮ ዞሮ ባለቤቱ ያስታውሰዋል: ነገር ግን የ110 ሚሊዮን ህዝብ አገር እንደዋዛ በጥፋት ጎርፍ እየተንሳፈፈ ባለበት አገር ችግሩ ከመሪዎች በላይ ነው:: የትግራይ ህዝብ እንደሆን እንኳን ከህዳሴ ግድብ ሊጠቀም ይቅርና ከተከዜ ግድብ ትንሽ መብራት እንኳን እንዳያገኝ ትራንስፎርመሩ ሳይቀር ደምስሰውታል:: ለ16 ወራት እንኳን መብራት መድሃኒትም የለም: ህዝቡ ከአለም ህብረተሰብ የተቸረለትን ምግብ እንዳያልፍ ተከልክሏል : ለመሆኑ ይህች አገር ባለቤት አላትን?
Abay Gedey (20 feb 2022)
Read More
|