INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት 2.6 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ገለጸ

ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ 2.6 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርም በተመሳሳይ በሀገሪቱ ባሉ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት 60 ገደማ ፕሮጀክቶች መቆማቸውን ገልጿል።

ተቋማቱ ይህን ያስታወቁት ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 6፤ 2014 ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ውይይቱን የጠራው፤ የፓርላማ አባላት በየተመረጡበት ምርጫ ክልል ከሚኖረው ሕዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ካቀረቡ በኋላ ነው። የፓርላማ አባላቱ በተወከሉበት አካባቢ ያለውን የመሰረት ልማት ጥያቄ የሰበሰቡት ባለፈው የካቲት በነበራቸው የዕረፍት ጊዜ ወደ ምርጫ ክልሎቻቸው በተጓዙበት ወቅት ነበር።

ከህዝብ ለተነሱት ለእነዚህ ጥያቄዎች ዛሬ ረቡዕ በፓርላማ ተገኝተው ምላሽ የሰጡት የመንግስት ተቋማት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው። እነዚህ ተቋማት ተጠሪነታቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ባለመሆኑ ሪፖርታቸውን በቀጥታ ለፓርላማው የማቅረብ ግዴታ የሌለባቸው ቢሆንም፤ መስሪያ ቤቶቻቸውን ለተመለከቱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ማብራሪያውን ካቀረቡት አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ፤ መስሪያ ቤታቸው በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት “ከፍተኛ ጉዳት” እንደደረሰበት ለፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል። “በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት በንብረት ብቻ ወደ 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኪሳራ ደርሶብናል” ያሉት አቶ ብዙወርቅ “በአማራ ክልልም፤ በአፋር ክልልም ስንደምረው ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶብናል” በማለት ጦርነቱ ወደ ሁለቱ ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ የደረሰውን የጉዳት መጠን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በበኩሉ በሀገሪቱ ባሉ ግጭቶች ሳቢያ የ60 ገደማ ፕሮጀክቶች ስራ መቆሙን ገልጿል። የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀብታሙ ተገኝ ፕሮጀክቶቹ 81 ቢሊዮን ብር ገደማ ዋጋ ያላቸው መሆናቸውን ለፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ተቋረጡ ያሏቸው ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው ምን ያህል እንደደረሰ እና የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።

የጸጥታ ችግሮች ፕሮጀክቶችን ከማስቆሙ ባለፈ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሰራተኞች ህይወት ለመጥፋት ምክንያት መሆኑ በዛሬው የፓርላማ ውሎ ተነስቷል። የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ፤ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ አካባቢ አራት የተቋሙ ሰራተኞች “በሽፍቶች” ተገድለዋል ብለዋል። “የእኛ ሰራተኞች እንደ ወታደር ናቸው። እየሞቱ ነው የሚሰሩት። አራት ሰራተኞቻችንን ገድለውብን አስክሬን ለማውጣት ሁሉ ተቸግረን ነበር” ሲሉ አቶ ሀብታሙ በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ ለፓርላማ አባላት አስረድተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እንዳይጀምር እንቅፋት እንደሆነበትም አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል። መስሪያ ቤቱ ከቡሌ ሆራ ሻኪሶ ያለውን መንገድ ለማሰራት ሶስት ጊዜያት ያህል ጨረታ ቢያወጣም ተጫራች አለመገኘቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ለዚህ በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ችግር “እዚያ አካባቢ ግጭት አለ፤ ሽፍታ አለ” ሲሉ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ “ተደጋጋሚ ጨረታ አውጥተን ነበር፤ አልተሳካም። ፍላጎት ያለው ሰው አልተገኘም” ብለዋል። “አሁን ለክልሉ ኢንተርፕራይዝ በቀጥታ ለመስጠት ድርድር እያደረግን ነው” ሲሉም መስሪያ ቤታቸው በስተመጨረሻ የወሰደውን አማራጭ አመልክተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)