INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

ርኢቶ - Point of View: ካሰች ጌታሁን

፩) ኣብ ልዕሊ ሰላማውያን ተጋሩ ዝተፈጸመ ግፍዒ ብ ናጻን ዘይሻራውን ዓለም ለኻዊ ኣካል ክጻረ ምውሳኑ፤

፪) እቲ ቓልሲ ህዝባው ቓልሲ (popular struggle)ኸምልኾነ ዓለም ምፍላጡ፤

፫) "እቲ ኹናት ዝጀመርዎ ሓይልታት ትግራይ 'ዮም" ልብል ናይ ስርዓት ብልጽግና ናይ ሓሶት ፕሮፓጋንዳ ተቐባልነት ምስኣን ("መን ጀመሮ" ኣብ ናይ ሕጊ ተሓታትነት ናይ ባዕሉ ጽልዋ ኣለዎ)፤

፬) ህዝቢ ትግራይ ል ጸላእቱ ከምዘይምብርከኽን ልናጽነቱ ብዙሕ ርሕቐት ኸምልጓዓዝ ኸምቲ ልሙድ ብተግባር ኣመስኪሩ፤

፭) ይቕረ በሃልነትን ዝሓለፈ ናይ ምርሳዕ "ጸገምና" (forgiveness & forgetfulness) ዋጋ ኽምዘኽፈለና [ብ 130 ዓማውቲ ልዕሊ ሽድሽተ ጊዜ ኸምልትወረርናን ክሕደት ኸምልትፈጸመ]፤

፮) ሓደ ል ሸውዓተ (1 to 7 ratio) ንቃለሶም ዘለና ፍልሖታት (human wave) ብ ኣውሮፓን ኤሽያን ኣድታት ዘይተረፈ ተሓጊዞም ምዃኑ፣ ጸላእትና ጥንካረን ጅግንነትን ህዝቢ ትግራይን ጥራሕ ዘይኾነ ናይ ውግእ ኣቕሞም 'ውን ኣጸቢቖም ኸምልፈልጥዎ ርዱእ ኾይኑ ኣሎ።

☛ ብዙሕ ስራሕ ልቕድሚት ይጽበየና 'ሎ። ኣብ ሓባራው ረብሓ (common ground/interest) ነትኹር። ዓወት ኣብ ኢድና ከምልትኣትው ፈጺምና ከይንጠራጠር። ብ ጽኑዕ ንቃለስ- tooth & nail!

ዓወት ልህዝቢ ትግራይ!

ሲገቡ መከራ ፣ ሲወጣ ፉከራ (ካሰች ጌታሁን)

ግጠሙን ይላሉ። ሲገጥሟቸው ወረሩን ይላሉ። ሲገቡ ወራሪ፣ ሲወጣላቸውን ፎካሪ ይሆናሉ። ብዙ ሆነው ይመጣሉ። ያለቀው አልቆ ፣ የተረፈው ቦታ ይቆጣጠራል። ብዙ ሰዎችን ማግዶ አሸነፍኩኝ ይላል።

በውሸት ሲፎክሩ ያስፈራሉ።ሲማረኩ እውነቱን ያወጣሉ። የሰው መሬት ሲይዙ እርስት አስመላሽ፣ መሬቱን ሲነጠቁ ድንበራችን ተጣሰ ብለው ይጮሀሉ። አንድ አገር እየሰበኩ ለክልላቸው ድንበር ያበጃሉ።

እነሱ ሲሳሳቱ በይቅርታ ይሰብካሉ። ሌላው ሲሳሳት ይቅርታውን የጥፋት ማስረጃ ያደርጋሉ። እነሱ ሲፈልጉ እንዋደድ ይላሉ። ካልፈለጉ ይጠላሉ። ፍቅር ፍቅር ይጨወታሉ። በድንገት ጨዋታውን አፍርሰው ጠላት ይፈጥራሉ። አጣልተው ያስታርቃሉ። አስቸግረው ይረዳሉ። በጥብጠው ሰላም ይፈጥራሉ።አስርበው ያበላሉ። አስጠምተው ያጠጣሉ። ልብስ ቀምተው ያልብሳሉ። አፈናቅለው መጠለያ ይሰራሉ። መጥፎ አድርገው መልካም ሆነው ይቀርባሉ።

በቅኝ ያልተገዛች አገር አለን ይላሉ። በአሜሪካ ይፈርሳሉ። በአሜሪካ ይጠገናሉ። ሲያስመስሉ አገራችንን ይወዳሉ። በእውነታው አሜሪካ ሄደው ይኖራሉ። ለአገሬ እዘምታለሁ ብለው ከአሜሪካ ይመጣሉ። መናፈሻ ደርሰው በፎቶ ይመለሳሉ። ለኢትዮጵያ ችግር ኢየሩሳሌም ይሳለማሉ። ለህዝባቸው ሀጥያት መካ ሄደው ይሰግዳሉ። ሲመለሱ እርስ በእርስ ይበጣበጣሉ።

ሰላም ሲባሉ ፈሪ፣ እነሱ ሲፈሩ ሰላም ይላሉ። ያሸነፉ ሲመስላቸው ሊያጠፉ ይመጣሉ። ሲሸነፉ አጠፉን ብለው ይጮሃሉ። አሳስተው ይመክሩሃል።እንድትደነቁር አደርገው ያስተምሩሃል። ከድንቁርናህ ለመውጣት ማሰብ ስትጀመር አጠቃኸን ይሉሃል።

አብሮ ለመኖር በትምክህት ይወጠራሉ። ስትሄድ ይፈራሉ። አጥቅተውህ ራስህን ስትከላከል አጠቃኸን ይላሉ። ስለአገር ሲያወሩ ትልቅ ሰው ይመስላሉ። ቆየት ብለው ባንዲራ ላይ ኮከብ ገባ ብለው በስእል የሚጣሉ ህፃናት ይሆናሉ። ታሪክ የሚሰሩት የሌላው ታሪክ በማጥፋት ነው። ከሰወወ ህሊና እናጥፋቸው ብለው የሰው አእምሮ ውስጥ ክፋትን ይሞላሉ።የራሳቸውን ታሪክ የሚያቆሙት፣ የሌላውን ታሪክ ተቆፍሮ እንዳይገኝ በመቅበር ነው። ሂዱ ተገንጠሉ ይሉሃል። ስትሄድ ይከቱሉሃል። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። አብረህ ብትኖር መከራ ነው። ብትለያቸው ፉከራ ነው።

Read More