INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

ፊንፊኔ መቼ ተወረረች እንዴትስ ተወረረች

በገዳ ስርዓት "ኦዳ ነቤ" ሥነ-ሥርዓት እሬቻ በድምቀት ከሚከናወንባቸው የኦሮሞ መሬት ክፍሎች ፊንፍኔ አንዷ ነበረች

ፊንፊኔ ተብሎ የሚታወቀው አካባቢና ዙሪያው ከኦሮሞ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የቱለማ ጎሣ ከሶስቱ ዐቢይ ጎሳዎች(“Balbala”) አንዱ የሆነው የዳጪ ንዑሳን ጎሳዎች የሆኑት የጉለሌ፣ የኤካ፣ የገላን እና የአቢቹ ጉሳዎች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፡፡

እነዚህ ጎሳዎች በ12 መንደሮች በመከፋፈልና በየራሳቸው የጎሳ መሪዎች ይተዳደሩ እንደነበር በወቅቱ የነበሩትን የጎሳ መሪዎች ስም በመዘርዘር ያስረዳሉ፡፡ ከእነዚህ የአካባቢ ጎሳ መሪዎች መካከል እነ ቱፋ ሙና፣ ዱላ ሃራ፣ ጂማ ጃተኒ፣ ጉቶ ወሰርቢ፣ ጂማ ጢቂሴ፣ አቤቤ ቱፋ፣ ዋሪ ጎሎሌ፣ ቱፋ አረዶ እና ሞጆ ቦንሳራ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በተለይም ፊንፊኔ የጉለሌ ኦሮሞ ጎሳዎች የሚበዙበት እንደነበረች በ1868 አካባቢ በካቶሊክ ሚሲዮኖች የተፃፉ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

በሌላ በኩል አፄ ሚኒሊክ ቤተ መንግስታቸውን በእንጦጦ ላይ ከማድረጋቸው በፊት በመስከረም 1868 ዓ.ም በፊንፊኔ አካባቢ ካቶሊክ ሚሲዮኖች “የፊንፊኔ ሚሲዮን” በሚል መጠሪያ ቤተክርስቲያንና የዕምነት ማስፋፊያ ጣቢያዎች ከፍተው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና በዚህም ፊንፊኔ በመልማትዋ ምንሊክ መቀመጫውን ወደ አከባቢው እንዲያዛውር በዋነኝነት እንደገፋፋቸው በወቅቱ የነበረ ሉዊፊ ላሴሬ የተባለው ሚሲዮን ፅፏል፡፡ ሌላው ምክንያት አፄ ሚኒሊክ አያታቸው “…አንቺ ምድር ዛሬ “…ች” ሞልተውብሻል፤ ነገር ግን ወደፊት የልጄ ልጅ ቤት ሰርቶብሽ ከተማ ትሆኛለሽ” በማለት ለባለቤታቸው ለእቴጌ ጣይቱ እንደነገራቸውና እቴጌም ባላቤታቸው ደቡብን ለመውረር በመጡበት ጊዜ ከባላቤታቸው ጋር ለጤናቸው ጉዳይ ወደፍል ውሃ ሄደው በነበረበት ወቅት ከነበሩበት ድንኳን ውጭ በመንዝ አካባቢ አይተው የማያውቁትን አበባ አይተው በመደነቅ አዲስ አበባ በማለታቸው ከ1887 ጀምሮ ፊንፊኔ – አዲስ አበባ መባል ጀመረች፡፡

የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የአከባቢዎችም ነባር ስያሜዎች ለውጥ/መቀየር አንድ ተብሎ ተጀመረ፡፡ በሚኒሊክ የጦር አበጋዞች በመላ ኦሮሞ አካባቢና የደቡብ አካባቢዎች ላይ አጠቃላይ ወረራ እስከታወጀበት እ.ኤ.አ 1870 በነበረው ጊዜ እርሻና ከብት እርባታን የኑሯቸው ዋነኛ መሰረት በማድረግ በፊንፊኔና አካባቢዋ ይኖሩ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጆች እንደተቀረው የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉ በገዳ ሥርዓት ይተዳደሩ የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ፊንፊኔ በኦሮሞ ክልል እምብርት ሥፍራ ላይ የምትገኝ መሆኗም የንግድና የአምልኮ ማዕከልም መሆን አስችሏታል፡፡

በገዳ ስርዓት ኦዳ ነቤ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ከሚከናወንባቸው የኦሮሞ መሬት ክፍሎች አንዷም ነበረች፡፡ ምንም እንኳን የፊንፊኔ ኦሮሞዎች በባህላቸው መሰረት ከራሳቸው፣ ከተፈጥሮና ከአካባቢያቸው ጋር ተስማምተው በዚህ ማዕከላዊ በሆነ ስፍራ ከቀደምት ክፍለ ዘመናት ጀምሮ በሰላም መኖራቸው የሚያጠያይቅ ባይሆንም በፊንፊኔና በዙሪያዋ በነበሩ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ላይ ከሰሜኑ አጎራባች ደጋማ ክፍል በሚነሱ ማህበረሰብ ተወላጆች ወረራና ዝርፊያ ይካሄድ የነበረው ሚኒሊክ የሸዋ ንጉስ ከመሆናቸውም አስቀድሞ እንደነበር በወቅቱ በስፍራው የነበረው የእንግሊዙ የዲፕሎማቲክ ልዑክ ሻለቃ W.C Harris [የኢትዮጵያ ደጋማ ክፍሎች The Highlands of Ethiopia, (1884)] በሚል ባሳተመው የጉዞ ማስታወሻ መፅሀፉ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በሂደት ወደ አጠቃላይ ወረራ የተቀየረውና በሚኒሊክ ወራሪ ጦር ድል አድራጊነት የተጠናቀቀው ዘመቻ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢውን የኦሮሞ ተወላጆች ለሞት፣ ለአካል መጉደልና ስደት ዳረገ፡፡ ከሞትና ስደት የተረፉት የመላ ኦሮሚያና የደቡብ ሕዝቦችም ነፃነታቸው ተገፎ በባርነት ቀንበር ስር ወደቁ፡፡ መሬታቸውን ተቀሙ፡፡ ሃብት ንብረታቸው በወራሪው ተዘረፈ፡፡ ግፍና በደሉ በዚህም አልበቃ ብሎ ፊንፊኔ ከወራሪው ጦር መቀመጫነት ወራሪውን ጦር ተከትለው የመጡ ነዋሪዎች መስፈሪያ ከተማ ሆነች፡፡ የፊንፊኔ ነባር ነዋሪዎች ከርስታቸው ተነቅለው ለወራሪው ሹሞች ተሰጡ፡፡ ለዚህ አስከፊ ተግባር ህጋዊ መሰረትና ድጋፍ ለመስጠት ሲባል በ1907 እ.ኤ.አ የመሬት አዋጅ (Land Charter) ተከትሎ በወጣው ማስታወቂያ የፊንፊኔ ነባር ኦሮሞዎች ካርታ ያልወሰደ በመሬቱ ከመቀመጥ በስተቀር መሬቱ ያንተ አይደለም ተባለ፡፡

የፊንፊኔ ነባር የኦሮሞ ተወላጆች በገዛ መሬታቸው ጪሰኛ ሆኑ፤ በእምነትና ባህላቸው መሰረት አምልኮአቸውን እንዳይፈፅሙ ታግደው የወራሪውን እምነት የመቀበል የመከራ ቀንበር በግዳጅ በላያቸው ላይ ተጫነ፣ ከዚህም አልፎ የጉለሌና የኤካ ጉሳዎች ሊመናመኑ ችለዋል፡፡ በወራሪው ጨቋኝ ገዢ የፊንፊኔ ነባር የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የወደቀው ግፍና መከራ በግድያ፣ በምርኮ፣ ከርስት መነቀልና በጭሰኝነት ጉልት ሥርዓት በማደር ብቻ ያበቃ አልነበረም፡፡ በኦሮሞ ተወላጅ ላይ እንደተጫነው የወራሪው ባህል ሁሉ በኦሮሞ ባህልና የቋንቋ ስያሜ ይታወቁ የነበሩ የፊንፊኔና ዙሪያዋ አካባቢዎች የከተሞችና የቦታ ጥንታዊ መጠሪያዎች እንዲቀየር ተደረገ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ፊንፊኔ የሚለው የጥንት መጠሪያዋ በሃይል ተቀይሮ “አዲስ አበባ” በሚል ስያሜ ተተካ፡፡

ፊንፊኔ መቼ ተወረረች እንዴትስ ተወረረች ወንድም ጉማ

Read More