INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

ኢትዮጵያ ለትግራይ ህዝብ የምድር ሶኦል ነች ማለት ስህተት ይሆን?

Politically correct ለመሆን መቸም ያልሆነው ነገር የለም:: የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የአለም-ህብረተሰብ ከዛሬ ነገ ይገባቸዋል እያልን ስንጠብቅ ወደ ለየለየለት የውሸት እንቅልፍ ተሸጋገረ:በነሱ አባባል " አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም " መሆኑ ነው::

በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጆነሳድ እስከ አሁን ካጋጠሙት የከፋ እንደሆነ በብዙዎች የተመሰከረለት ስለሆነ አዚሁ መዘርዘር አያስፈልግም::

የትግራይ ሰራዊት በህዝቡ ላይ የደረሰውን ሁለንተናዊ ግፍ ለመታደግ ወደ አዲስ አበባ ባመራበት ሳምንት የአለም መንግስታትና ኢትዮጵያዊያን ኡኡታ አሰሙ: ከውጭና ከውስጥ ተሰባስበው አማራ ተወረረች ኢትዮጵያ ተቀበረች ብለው ትግራይ ሌላ ወራሪ አገር እንደሆነች አስመስለው : ወደ ስልጣን ያመጣቸውን አሜሪካም ጭምር አፍሪካን እንደወረረ የሚመስል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሰርተው " TDF ሆይ ወደ አገርህ ተመለስ ብለው ተማፀኑ::

የትግራይ መንግስትና ሰራዊት ለሰላም እድል እንስጥ: ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ከወታደራዊ ድል ጋር ካልተጣጣመ አገር ያፈርሳል በሚል ሃላፊነት በተሞላበት ውሳኔ ወደ ትግራይ ሲመለሱ : የአብይ ሰራዊት ትከትሎ ለማጥቃት ያደረገው ሙከራ ለተጨማሪ እልቂት ከተዳረገ በኋላ የተለቀቁት ቦታዎች ነፃ አወጣሁ ብሎ የተለመደው የቴሌቭዥን ድራማ ሰራና "ወደ ትግራይ አንገባም አቁመናል" አለ::

ይህን ሁሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብ እስከአሁን ድረስ በከፊል ነፃ አልወጣም:

የኢትዮጵያ የአማራና ኤርትራ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች በግፍ እየተገደሉ ነው:ሴቶች እየተደፈሩ ነው::

የእርዳታ ምግብና መድሃኒት እንዳያገኝ ተከቦ ህፃናትና አዋቂዎች በረሃብ እያለቁ ነው::

ይህን ሁሉ አልበቃ ብሎ በየቀኑ በአየር ድብደባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን እየሞቱና እየቆሰሉ ነው::

ከሁሉም በላይ የሚያናደድውና የዚች አገር ህዝብ ስብእና ጥያቄ ውስጥ የሚከተው ህዝቡ የመሪዎቹ የእነ አብይና ዳንኤል ክብረት መሳሪያ መሆኑ ነው:: በትግራይ ህዝብና በተለይም በሴቶች ላይ የደረሰው የአንድ አመት ሙሉ ሞትና ስቃይ ከምንም ሳይቆጥር በአማራ ክልል አዲስ የሴቶች ጥቃት ድራማ እየተሰራ መመልከቱና በውሽት ትርክት የትግራይ ህዝብ ስቃይ ለመደምሰስ (false equivalence) ለመፍጠር መሞከሩ ነው::

በዚህ የፈረንጆች አዲስ አመትና በአለ-ልደት ሌላው ህዝብ ኬክ እየቆረጠና ከቤተሰቡ ጋር እየተዝናና የትግራይ ህዝብ ግን በረሃብና በአየር ድብደባ የቁም ስቃይ እያየ ነው: እውነት ሶኦል ካለ በመሬት ላይ ከዚህ የባሰ ምን ሲኦል ሊኖር ይችላል?

ከአንድ አመት በላይ የትግራይ ህዝብ የጨፈጨፉት ወንጀለኞች የኢድ አሚን እኩያ ሆንው የፊልድ ማርሻክ መአረግ ሲሸለሙ ማየት በኢትዮጵያ ምድር ለሚኖር የትግራይ ህዝብ ሶኦል ከመሆን የተለየ ምስ ስም ይሰጠዋል?

ካለ ምንም ምክንያት የታሰሩትና ከ70ሺ በላይ የሚገመቱ ተጋሩ የቁም ስቃይ በሚያዩባት አገር 6 እስረኞች ፈትተናል ብለው 6 ሚሊዮን ህዝብ ለሞት የሚዳርግ አገር ምን ስያሜ ይሰጠዋል ?

እኔ እስከ አሁን ከሰማሁት የስቃይ ቤት በሃሳብ የመጣልኝ ሲኦል ነው: ኢትዮጵያ ለትግራይ ህዝብ ሲኦል ነች!

የትግራይ ህዝብ ግን በሲኦል መኖር የማይገባው ወደ ገነት የሚሸጋገር ህዝብ ነው: ቃሉ ከእምነት ጋር ላያይዘው አልፈልግም: የመሬት ላይ ሶኦል ያልኩትም ለዚህ ነው::

የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ባሳየው አስገራሚ ፅናት ታግሎ ጠላቶቹ እያሽነፈ ነው: የመሬት ሲኦል የሆነችው ኢትዮጵያ እንጂ ትግራይ እንኳን ለትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ምርኮኞች ገነት ሆናለች::ሊገድሉት የመጡና የተማረኩ ሃይሎች በጥሩ ሁኔታ መያዛቸው ብቻ ሳይሆን ውደ ቤተሰቦቻቸው ህልውናቸው የሚገልፁበት የቴሌቭዥን (TMH) መስኮት መኖሩ አለምን አስገርሟል::

የትግራይ ሰራዊት ከሃገረ ገነቷ ትግራይና ህዝቧ የወጣ ህዝባዊ አላማ ያለው ባይሆን ኖሮ : ወይም በትግራይ የደረሰውን ጥፋትና ውድመት የሚበቀል ቢሆን ኖሮ: ከወልድያ እስከ ኮምቦልቻ በቆየበት ሳምንት ፋብሪካዎች ብቻ ሳይሆን ከተሞችን ማቃጠል የሚችልበት አቅም ነበረው: በተቃራኒው ከተሞቹ ከፋኖ ወረበሎች ጠብቆ ነው በሰላማዊ መንገድ የለቀቀው:: መንገድ መዝጋትና በግና እህል መዝረፍ የለመደው ፋኖ ላደረሰው ጥፋት TDF ለምክሰስ መሞከራቸው ግን ትእግስት ያስጨርሳል::

በትግራይ ህዝብ ላይ ያልደረሰ/ያልተፈፀመ ግፍ አለ ብየ አልገምትም :: የትግራይ ህዝብ አንድ የሚስማማበት ጉዳይ ግን አለ:: የዚች ሳምንት የሰላም እድል የማይሰራ ከሆነ TDF የተለመደው ተአምር ያሳየን ይሆናል::

ትግራይ ታሸንፋለች!

Read More