ወራሪ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የአማራ፣ የሶማልያ ሰራዊቶች በትግራይ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1570503729979716&id=100010603118739
ወራሪ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የአማራ፣ የሶማልያ ሰራዊቶች በትግራይ
በቆዩባቸው ወራት በትግራይ የነበሩ ፋብሪካዎችን ሙሉ ለሙሉ ነው ያወደሙት።
በተለይም ረሐብተኛው የኤርትራ ሰራዊት ከአልመዳ፣ አዲግራት መድሐኒት
ፋብሪካ፣ ጎዳ የብርጭቆ ፋብሪካ፣ ሼባ ሌዘር፣ ሰማያታ እምነበረድ፣ ኢዛና
የመአድን ፋብሪካ፣ ስፓ ውሐና ሌሎች ፋብሪካዎች ማሽነሪዎችን ነቃቆሎ ነው
የወሰደው፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ በድማሚት አውድሞታል።
የአማራ የትምክሕትና የጄኖሳይድ ሐይልም እንዲሁ በምዕራብ ትግራይ የነበሩ
የኢንዳስትሪ ተቋማት(የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ) ሙሉ ለሙሉ ወደ
አመድነት ቀይረዋቸዋል። የኢትዮጵያ ሰራዊትም እንዲሁ በንፅፅር ደረጃው አነስ
ባለ መጠንም ቢሆን ተመሳሳዩን ፈፅሟል።
እነዚህ ፋብሪካዎች አሁን ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፤ እንደ አዲስ ካልተሰሩ በቀር
ሊጠገኑ የሚችሉም አይደሉም፤ ሙሉ ለሙሉ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
"አማራን አወደመ" የተባለው የትግራይ ሰራዊት ግን የኮምቦልቻ የኢንዳስትሪ
መንደርን ሲጠብቅ ከረመ፤ እነሆ ከኢንዳስትሪው መንደር የተበላሸ ወይም
የተዘረፈ አንድ ወሳኝ ማሽን ወይም ሌላ ወሳኝ ግብአት እንኳ ባለመኖሩ ይኸው
በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ሊገባ ነው። ይህንን የኢትዮጵያ መንግስት
ሚድያዎችም እያረጋገጡት ነው።
የትግራይ ሰራዊት ኮምቦልቻን የለቀቀ ቀን የከተማው ወጣቶች የኢንዳስትሪ
መንደሩ ላይ የተወሰነ ዝርፍያ የፈፀሙ ቢሆንም የተወሰኑ የቢሮ እቃዎችና ጥሬ
እቃዎች ነው የዘረፉት። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ይህንን ተራ የመንደር ዝርፍያ
በትግራይ ሰራዊት የተፈፀመ የኢንዱስትሪ መንደሩንና ከውስጡ ያሉ
ፋብሪካዎችን የማውደም ስራ" አስመስለው እያቀረቡት ነው፤ ገና ብዙ ብዙም
ይላሉ። ፍፁም ሐሰት እንደሆነ ግን የኮምቦልቻ ህዝብ ያውቃል፤ ህሊና ያለው
ሁሉ ሊያገናዝበው የሚችል ቀላል ሐቅም ነው።
በአጠቃላይ ከኢንዳስትሪ መንደሩ አንድ የተበላሸ የፋብሪካ ማሽን፣ አንድ የወለቀ
ብሎን የለም፤ ፋብሪካዎቹም ሰሞኑን ወደ ስራ እንደሚገቡ እየተገለፀ ነው።
እናስ የትግራይ ሰራዊት የአማራ ጠላት ነውን?
የሚባለውን፣ የሚወራውን ሳይሆን አይናችን የሚያየውን ነው ማመን ያለብን።
የትግራይ ሰራዊት ቢፈልግ የኢንዳስትሪ መንደሩንና ከውስጥ ያሉ በርካታ
ፋብሪካዎችን ልክ የኤርትራ፣ የአማራና የኢትዮጵያ ሰራዊቶች እንዳደረጉት ወደ
አመድ ክምርነት፣ ወደ ፍርስራሽነት መቀየር አይችልም ነበርን? እስቲ ያንን
ለማድረግ ማን ከለከለው?
via ztseat save ananya
Read More
|