INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የዓዲ ግራት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ግንኙነቶች ማቆሟን አስታወቀች

የዓዲ ግራት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምንም እንኳ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ባይኖራትም ከአስተዳደራዊ እና ስብከተ ወንጌል ጋር የሚገናኙ ቀጥተኛ ያልሆኑ ግንኙነቶች ማቆሟን አስታወቀች

በኢትዮጵያ የሚገኙ ሃይማኖት ተቋማት በፋሽስታውያን እና ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውና እየተፈፀመ ያለው ጄኖሳይድ እንዲቆም ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን አለመወጣታቸው የሚያሳፍር እና የሚወቀስ መሆኑን የዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሀገረ ስብከት አስታወቀች።

ቤተ ክርስትያኗ ባወጣችው ወቅታዊ መግለጫ ቀጥታ ተጠሪነቷም ሆነ ግንኙነቷ በሮም ለምትገኘው አለም አቀፍ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በስብከተ ወንጌል እንዲሁም ካቶሊካውያንና አገልግሎት ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር በጋራ እየሰራች መምጣቷን የመቐለ ልደታ ለማርያም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቆሞስ አባ ጥዑም በርሀ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በትግራይ ህዝብ ላይ ከሰብኣዊነት የራቀ እጅግ ዘግናኝ ግፍና ጭፍጨፋ ሲፈፀም ጉዳዩ በቶሎ እንዲቆም እ ተፈፀመ ያለው ጄኖሳይድ እንዲያበቃ ቤተ ክርስትያንዋ በተደጋጋሚ መጠየቅዋን ገልፀዋል።

ቤተ ክርስትያንዋ ምንም እንኳ ከኢትዮጵያ ካቲሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ባይኖራትም ከአስተዳደራዊ እና ስብከተ ወንጌል ጋር የሚገናኙ ቀጥተኛ ያልሆኑ ግንኙነቶች ማቆሟን ኣበ ጥዑም በርሀ ገልፀዋል።

የካቲት 16/2014 ዓም
Digital Weyane ዲጂታል ወያነ

Read More