ራስ አሉላ አባነጋ (አፍሪካዊ የጦር ጀኔራል)
ዶግዓሊ - 135ኛ ዓመት የድል መታሰቢያ
ጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ የመጀመርያው አፍሪካዊ ጀነራል በመባል የሚታወቁ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ቱርክን እና ጣልያንን በተደጋጋሚ ያሸነፉ የተሳካለት እንዲሁም በአለም የተመሰከረላቸው ወታደራዊ መሪ እና ተዋጊ ናቸው።
ነ’ጭ ወራሪዎች፣ በጥቁር ህዝብ በጦርነት ለመጀመርያ ጊዜ የተሸነፉት በጥር 18 እና 19/1879 በግእዝ አቆጣጠር (25 & 26 Jan, 1887 በፈረንጅ አቆጣጠር) ማለትም ልክ ከ135 ዓመት በፊት “በሰሐጢ” እንዲሁም “በዶግዓሊ” በተካሄዱ ጦርነቶች ሲሆን እነዚህ ጦርነቶች የመሩት ደግሞ ታዋቂው የአፄ ዩሀንስ ወታደራዊ አመራር እንዲሁም የምድሪ ባሕሪ (የአሁን ኤርትራ) ገዢ ራስ አሉላ አባነጋ ከሰራዊታቸው (የትግራይ ሰራዊት) በመሆን ነበር ያሳኩት።
ራስ አሉላ አባነጋ የቤት ስማቸው አሉላ እንግዳ ቁቢ (ባሻይ) ሲሆን በትግራይ ተምቤን ዓብይ ዓዲ “ዙቕሊ” የምትባል ቦታ ነው የተወለዱት፣ መኖርያቸው ደግሞ “መነወ” በሚባል አካባቢ ነበር። እድምያቸው ለትምህርት ሲደርስ እንደ ማንኛውም የትግራይ ልጅ ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ገቡ፣ አባታቸው እንግዳ ቁቢ ለልጃቸው አሉላ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ከመንፈሳዊ ትምህርት ጎን ለጎን ፈረስ ግልብያ፣ ቶክስ (ኢላማ)፣ ዉሀ ዋና የመሳሰሉት ያስተምሯቸው ነበር። በወጣትነት እድምያቸው ትግራይ ውስጥ የሰራዊት አባል ሆነው እያገለገሉ ሳሉ በወቅቱ የኢትዮጲያ ንጉስ አፄ ተክለጊዮርጊስ የማረኳቸው (የትግራይ ህዝብ ለማስገበር ከአፄ ዩሀንስ ጋር በተደረገው ጦርነት) እሳቸው ናቸውም ይባላል። “አባነጋ” ማለት አፄ ዩሀንስ ስም ያወጡለት እንዲሁም በስጦታ መልክ ለራስ አሉላ የተሰጣቸው ፈረስ ሲሆን፣ “ምሕረት” ደግሞ የታሪካዊቷ ጠበንጃቸው ስም ነው።
ራስ አሉላ አባነጋ በብዙ ጦርነቶች ከባዕዳውያን ወራሪዎች በጀግንነት ተዋግተው እንዳሸነፉ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት፣ የልጅ ልጆቻቸው (የትግራይ መከላከያ ሰራዊት) ከፋሽስት የኢትዮጲያ መንግስት፣ ተስፋፊ የአማራ ሀይሎች፣ የኤርትራ መንግስት፣ ዓረብ ኢምሬትስ እና ሊሎች በቀጥታ የተሳተፉበት ወረራና ጦርነት በጀግንነት፣ በፅናትና በሚያስደንቅ መልኩ ታሪኩን እየደገሙት የመጡ ሲሆን ቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት የታወቀ ነው።
የዶጋዓሊን ጦርነት አስመልክቶ ለራስ አሉላ አባ ነጋ የተገጠሙ ግጥሞች
1. መብቱን ዩሀንስ ላሉላ ቢሰጠው
እንደ ቀትር እሳት ቱርክን ገላመጠው
ጣልያንም ወደቀ እያንቀጠቀጠው
አጭዶና ከምሮ እንደ ገብስ አሰጣው።
አባ ነጋ አሉላ ካስመራ ቢነሳ
እንዳንበሳ ሆኖ እሳት እያገሳ
የችግር ምስጋና ባይወሳ
ቢቸግረው ጣልያን አለ ፎርሳ ፎርሳ።
ጣልያን በሃገርህ አልሰማህም ወሬ
የበዝብዝ አሽከሮች እነሞት አይፈሬ
ዘለው ጎብ ይላሉ እንደ ጎፈር አውሬ።
አባ ነጋ አሉላ የደጋ ላይ ኮሶ
በጥላው ያደክማል እንኳንስ ተቀምሶ።
ጣልያን ሰሐጢ ላይ እግሩን ቢዘረጋ
በብረት ምጣዱ በሰሐጢ አደጋ
አንደርድሮ ቆላው አሉላ አባ ነጋ።
ተው ተመከር ጣልያን ይሻላል ምክር
ሰሐጢ ላይ ሆነህ መሬት ብትቆፍር
ሃላ ይሆንሃል ላንተው መቃብር
ይቺ አገር ኢትዮጲያ የበዝብዝ አገር
ምንም አትቃጣ እንዳራስ ነብር።
2. ሓሽከር ፈንቅል ዝበለ ገባሪ
ሓሽከር በዝብዝ ዝበለ ገባሪ
ጎይታ ሓማሴን ጎይታ ቁሪ
ጎይታ ዓሳውርታ ገምገም ባሕሪ
ወደረኛ ጣልያን በዓል ምስሪ
ወደረኛ ቱርኪ በዓል ምስሪ
ወደረኛ ድርቡሽ ሓጀ ኑሪ
ሓፂርን ነዊሕን ንሓደ ዘማዕሪ
ይውሕጠና ዝብሉኻ ከም ባሕሪ
የንድደና ዝብሉኻ ከም ጓህሪ
ከም ኣንበጣ ኣብ ጎቦ ሰፋሪ
መጋረጃ ሓበሻ መቑሕ ቁሪ
ድፍእ የብሉኻ መነደሪ
ኩዒትካ ትቐብሮም ትሕቲ ቁሪ
መሓር ኢሎምኻ ዘይምሓሪ
ግበር ኢሎምኻ ዘይገባሪ
ኣብ ልብኻ ትፅሕፋ ነታ ምኽሪ
በኡነትዶ ውሒጡካ ምድሪ
ከም ኣባ ነጋ ዝበለዶ ኣብ ኣምበራ ይቐሪ
ብእግዚኣብሄር ድኣ ኮይኑ ብፈጣሪ።
3. ጮማ ተበሊዑ ኢልኩም ኣይትህረፉ
ነጪ ተበሊዑ ኢልኩም ኣይትህረፉ
ሜስ ተሰትዩ ኢልኩም ኣይትህረፉ
ያባትን አልጋ መስጠት ነው ክፉ
ሓፂር ዓጢቕኩም ግዳ ተራገፉ
ኣባ ነጋ ኣሉላ እንድሕሪ ደጊፉ
ሓለቓ ሰናዲር ፀቢብ ኣፉ
ምእይቲ ዓመት ትገዘኡ ውዝፉ።
4. ክንሰምዖም ደሞ ኣባ ጎይታና
ላዕሊ ምቕማጦም ከም ደበና
ንድኻ ይፀንሕዎ ብትሕትና
ንሓያል ይፀንሕዎ ብልዕልና
ናይ ልቦም ዝገብሩ ከም እግዚኢና
ናይ ዶድዓሊ ዶሞ ክነግረሎም ዜና
ሕርድ ወዓልዎ ንበዓል ጣልያና
ናይ ኮፊት ዶሞ ክነግረሎም ዜና
ድርቡሽ መፀት ክትመስል ደበና
ናይ ኣባ ነጋ ወረ ዶኾን ዘይሰምዐት ኮይና
ልብን ድርዕን ኩላ ተኸዲና
ርእሳ ሰበርካያ ከም ሽክና
ዓፅሚ ኣዳም ሰራሕኻዮ ኳና
ኣብ ሓመድ ኣሕደርካዮ ንኦቶማን ጅግና።
Read More
|