INFORMATIE EN GEGEVENSVERZAMELING VOOR ONAFHANKELIJKE TIGRAY

ኣብዚ ገጽ እዙይ ብተጋሩ ልተጽሓፈ ተግንዩ

ዝርዝር ኣዋርሕ ኣብ ጎኒ እኒሀኩም። መጀመርታ ወርሒ ምረጹ ድሕሪኡ ልትደልዩዎ ኣረስቲ (ጽሑፍ) መሪጽኹም ኣንብቡ።

የሀሰት አንድነት ሰባኪ አሀዳውያን ልዩ መለያ....

1,"አንድነት" የሚሏት ቃል ከፖለቲካ ቋንቋቸው የማትለይ "ሀይማኖቱ" ትሆናለች፡፡
ይደጋግማታል፡፡አዘውትሮ ያነሳታል፡፡በእርሷ ምሎ በርሷ ይገዘታል፡፡ ሆኖም "አንድነት እንዴት? " የሚለውን ጥያቄ በተግባር መመለስ የማይችለውን ያህል በሀሳብ ፈጽሞ አይፈልገውም፡፡

2,ስልጣኑን ከተወሰነ ሀይማኖት ጋር ይያያዛል፡፡የእርሱ ገዢነት ሲቀር የአምላኩ ቁጣ የወረደ ይመስል በየቤተ እምነቱ "ጹሙ፣ጸልዩ...ፈጣሪን ይቅር በለን በሉ" እያለ ስነ-ልቦናዊ ሽብር ያስፋፋል፡፡

3,በተፈጥሮ ለመግዛትና ለመገዛት የተፈጠረ ህዝብ ያለ ይመስል የገዢዎቹን ግለሰቦች የዘር ሀረግ ከታወቀ "ዘር " ጋር ያገናኛል፡፡(የሰለሞን ዘር የተለመደች ናት)

4,ሀይማኖትን በመሳሪያነት ይጠቀማል፡፡ በወረራ የያዘውን ህዝቦች የሀይማኖቱ አማኝ በማድረግ ስነ ልቦናዊ አቋሙን ከራሱ ጋር ለማቆራኘት ይሞክራል፡፡ክልሉን ወደ ራሱ የሀይማኖት ደሴትነት ይቀይራል፡፡

5,በቋንቋው ከመጠን በላይ ይመካል፡፡ያስፋፋል፡፡በሌሎች ህዝቦች ቋንቋዎች ላይ ያላግጣል፡፡ዝቅተኛ አድርጎ ያያቸዋል፡፡በት/ት ቤቶች በፍርድ ቤቶች መስሪያ ቤቶች የራሱን ቋንቋ የበላይነት ይገነባል፡፡የራሱ ቋንቋ ብቻ የሀገሪቱ ቋንቋ እንዲሆን ብቻ ይሻል፡፡ ሌላው "የኔስ" በማለት ከተነሳ የተለያየ ማጥላላት ዘመቻ ይፈጽማል፡፡

6,ባህሉን ሀገር አቀፋዊ አስመስሎ ዬቀርባል፡፡ የሌሎችን ያንቋሽሻል፣ይንቃል፡፡

7,የሌሎችን መብት መቀበሉ ቀርቶ መስማቱ እንኳን ያንገሸግሸዋል፡፡ የአንድነትን እና እኩልነትን የማይነጣጠሉ ባህሪያት ስለየማይቀበል እኩልነትን ጨቁኖ አንድነትን ይፈልጋል፡፡

Read More