INFORMATION AND DATA COLLECTION FOR FREE TIGRAY

In this page you find Reference docs (in books or pdf form) about Tigray.

On the sidebar, at the right side of this page, click on the month and then the title of the article of your interest to read.

Pubblished by NY Times 15 ctober 2021
Title: ሰሜን እዝ በተኛበት ተወጋ የሚለው ድርሰት ጊዜው ያበቃለት ይመስላል።
Links Click here to read copy of the document in English

ሰሜን እዝ በተኛበት ተወጋ የሚለው ድርሰት ጊዜው ያበቃለት ይመስላል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት በትግራይ ህዝብ ላይ ለተከፈተው ጦርነት መንገድ እንደሆነ የሚገልፅ የThe New York Times ዘገባ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ይዞ መጥታል። በትግራይ ህዝብ ላይ ወረራ ከመፈፀሙ ወራቶች በፊት፣ በፋሽስት አብይ እና ኢሳያስ ወታደራዊ ዝግጅቶች እንደነበሩ በዚህ ዘገባ ተረጋግጧል። አንድአንድ ነጥቦች ከዘገባው፦

- አብይ እና ኢሳያስ የሰላም ስምምነቱ ከተፈራረሙበት ጊዜ አንስቶ በትግራይ ወረራው እስኪፈፅሙ ድረስ ቢያንስ 14 ጊዜ እንደተገናኙ፣ ሁሌም ስብሰባዎቹ አንድ ለአንድ (አብይ እና ኢሳያስ ብቻ) እንደነበሩ

- በተጨማሪም አብይ እና ኢሳያስ በድብቅ ይገናኙ እንደነበር፣ ከ2019 እስከ 2020 ቢያንስ ከ3 ጊዜ በላይ በድብቅ እንደተገናኙ

- ህዳር 9/2011 ኢሳያስ ጎንደር ከተማን ጎበኘ፣ ከዚህ ወቅት ጀምሮ የኤርትራ መንግስት ሰዎች በተደጋጋሚ ወደ አማራ ክልል መመላለስ እንደጀመሩ

- በኋላም የኤርትራ ዘፋኞችና ዳንሰኞች (የኪነ ጥበብ) ቡድን አማራ ክልልን ጎበኙ። በዚህ የልዑካን ቡድን የኤርትራ የስለላ ሃላፊ አብርሃ ካሳ ከአማራ ክልል ሰዎች ጋር ለመገናኘት እንደተጠቀመበት

- ኤርትራ 60,000 የአማራ ልዩ ሃይል የተውጣጣ ወታደሮችን ለማሰልጠን ተስማማች፣ ሰለጠኑ በኋላም ወደ ትግራይ እንደዘመቱ

- በዝግ ቤት፣ የፋሽስቱ አማካሪዎቹ እና የጦር ጄኔራሎቹ ስለ ትግራይ ወረራ ጉዳይ ተወያዩ፣ ተከራከሩ። በወረራው እቅድ ያልተስማሙት ተባረሩ፣ ሽጉጥ ተደቅኖባቸው ተመረመሩ ካልሆነ ደግሞ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ እንደተደረጉ

- ከተቃዋሚዎቹ መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ ጀነራል አደም መሐመድ ይገኙበታል

- ከትግራይ ምርጫ በፊት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ጭነት አውሮፕላኖች በሌሊት ወደ ኤርትራ የጦር ሰፈሮች በድብቅ በረራ እንደጀመሩ

- ህዳር 2013 ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ባሉት ወራቶች ውስጥ አብይ ወታደሮቹን ወደ ትግራይ አጎራባች ክልሎች እንዳንቀሳቀሰ

የቀድሞ የአብይ አስተዳደር ባለስልጣን የነበረው አቶ ገብረመስቀል ካሳ:-

- ከኖቤል የሰላም ሽልማት በኃላ “አብይ በአለም ላይ ካሉት ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች አንዱ እንደሆነ ይሰማው ነበር” ሲል በቃለ ምልልስ ተናግሯል

- “ብዙ አለም አቀፍ ድጋፍ እንዳለው ተሰምቶት ነበር፣ እና ወደ ትግራይ ጦርነት ከገባ ምንም እንደማይሆን ተሰምቶታል” ሲል አክሏል

- ጥቅምት 2013 በተዘጋጀው የብልፅግና ባለስልጣናት ቪድዮ ኮንፈረንስ የትግራይ መንግስት (አመራሮች) ለመያዝ ከ3-5 ቀናት ብቻ እንደሚፈጅበት እንደገለፀላቸው በዘገባው ተገልፇል::

- ሌሎችም...

የጦርነቱ መንስኤ "ሰሜን እዝ በተኛበት ተወጋ" የሚለውን ድርሰት እንዳልሆነ የአለም ማህበረሰብ መገንዘብ እና ማረጋገጥ መጀመሩ ይበል የሚያስብል ጅማሮ ነው::

የትግራይ ህዝብ በትግሉ ጠላቶቹን በሙሉ ያሸንፋል!
ድል ለትግራይ ህዝብ!
ድል ለትግራይ መከላከያ ሰራዊት!

Read More